Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለኛ ዙር በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለገጠር ቀበሌዎች የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን (ፈርኒቸር)፣ አላቂ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ና ለገጠር ቀበሌዎች የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የፅዳት ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን (ፈርኒቸር)፣ አላቂ ዕቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጸውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።

5. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ካልቀረበ እና ማንኛውም ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱ የተጫራቹ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።

6. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል እንዲሁም የዱግዳ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ መሞላት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ (Lot) 5000 (አምስት ሺህ) በCPO ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኃላ በገበያ ጥናት ውስጥ እና አሸናፊ ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚሰጥ ዋጋ ይሆናል።

9. ተጫራቾች የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦሪጅናል (original) መሆን ይኖርባቸዋል።

10.የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይቻላል።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርበቸዋል።

12.የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል።

13. አሸናፊው ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ለጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለመሰሪያ ቤቱ ውል ማሰከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

14. ማንኛውም ተጫራች መሰሪያ ቤቱ በሰጠው የናሙና ዝርዝር ዕቃዎች መሰረት በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅበታል።

15. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማሰከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና 1/2009 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር 157/2002 መሰረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል።

16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 13 85 13 91/ 09 32 31 91 92 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አድራሻ፡- በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳደር የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳድር የዱግዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በ6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-09 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Shewa Zone Adminstration Dugeda Woreda FEDB
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T07:44:44.000Z
← Back to all tenders