Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001_/2019 ዓ.ም

የየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በተቋሙ ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ጽ/ቤቶች የሚውል፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የደንብ ልብሶች እና የፅዳት እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች

1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ እንዲችሉ የግብር ግዴታቸውን ስለመውጣቸው የተሰጠ የምስክር ወረቀት ለተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ እና በተጨማሪ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቅት ማቅረብ አለባቸው፣ የሚቀርበው ሰነድ የሚታይ መሆን አለበት።

2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታይ የስራ ቀናት ክፍት መሆኑን እየገለፅን በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከታች በተገለፀው አድራሻ ጨረታው በሚዘጋበት ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ዘገይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ወድቅ ይሆናል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን የማይመለስ የሰነድ መሸጫ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በእያዳንዱ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠባቅባቸዋል።

5. ተጫራቾች የሚመረቱበትን የእቃ አይነት የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን ሲያስገቡ ከቋሚ እቃ በስተቀር ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ያለ ናሙና የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

6. አድራሻችን ኮተቤ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ ወይም ሰንሻይን መንደር ፊት ለፊት ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ዋ/የስራ ሂደት ክፍል ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ስልክ ቁጥር 011 893 169 በመደወል የሚፈልጉትን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።

ማሳሰቢያ፦ ተቋሙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 12 አስተዳደር ፋ/ ጽ/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 12 Adminstration FEDB
  • Bid bond: 15000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T07:52:00.000Z
← Back to all tenders