Stationery

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የህትመት፣ ኤሌክትሮኒከስ እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ስራዎች እንዲሁም የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በስሩ ላሉት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ቋሚና አላቂ እቃዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣
  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ፈርኒቸሮች፣
  • የመኪና ጎማዎች፣
  • የህንጻ መሳሪያዎች፣
  • የደንብ ልብሶች፣
  • የህትመት፣ ኤሌክትሮኒከስ እና
  • የተሽከርካሪዎች ጥገና ስራዎች እንዲሁም
  • የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት ትችላላችሁ።

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የተሰማሩበት ወይም ተጓዳኝ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚውል ከታወቀ መንግታስዊ ባንክ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በCPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ መግዣ በሮቤ ከተማ ዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከሮቤ ከተማ ዜይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።
  5. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት እውቅና የተሰጣቸውን እቃዎች የሚያቀርብ መሆን ይኖርበታል።
  6. ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣የኮምፒውተር ቀለሞች ፣ቦርሳዎች ጨረታ ከመክፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ማቅረብ አለበት።
  7. ለሰራተኞች ደንብ ልብስ የሚሆን ብትን ጨርቆች የተዘጋጁ ልብሶችና የተለያዩ ቆዳ ጫማዎች ለከፋይ ምንጣፍና ለጨርቅ መጋረጃ እና ቀለሞች ናሙናዎች በሙሉ ለብቻ በፖስታ አሽገው ጨረታው ከመክፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና እቃውን ማቅረብ አለባቸው።
  8. በሰነዶቻቸው ላይ ሥማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  9. የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
  10. በተገለጹት የእቃ ዝርዝሮች አጠገብ በተቀመጡት ባዶ ቦታዎች ላይ የእቃዎችን ብራንድና ሞዴል በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል።
  11.  በሚጫረቱት ሰነድ ላይ ከተገለጸው ስፔስፍኬሽን ውጪ በመሰረዝና በመደለዝ የራስን ስፔስፍኬሽን መጨመር አይቻልም አማራጭ ካላቸው ግን የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት በመጥቀስ ለብቻ በሌላ ወረቀት ማያያዝ ይችላሉ።
  12. ለሁሉም እቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  13. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይቻልም።
  14. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
  15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታውን ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውሉ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  16. የሚገዙ እቃዎች በተሰጠው ስፔስኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ኦሪጂናል ካልሆኑ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተከፍቶ ውሉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግዢ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ይሆናል።
  18. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሚሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 09 16 60/ 9 66 66 71 76 ደውለው ይጠይቁ።

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የዘይበላ ወለሼ ክ/ከ/ገንዘብ/ ጽ/ ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 3፡30
  • Bid opening: 2026-09-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጠበት ቀን አንስቶ ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ዘይበላ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T08:06:59.000Z
← Back to all tenders