Stationery

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የመኪና ጎማዎች የህንጻ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የህትመት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ስራዎች እንዲሁም የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት በስሩ  ሌሎት ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ

  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ቋሚና አላቂ እቃዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣
  • የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ፈርኒቸሮች፣
  • የመኪና ጎማዎች፣
  • የህንጻ መሳሪያዎች፣
  • የደንብ ልብሶች፣
  • የህትመት፣
  • ኤሌክትሮኒክስ እና የተሽከርካሪዎች ጥገና ስራዎች
  • እንዲሁም
  • የምግብ አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች የምታሟሉ ተጫራቾች መጫረት

  1. በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ የተሰማሩበት ወይም ተጓዳኝ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚውል ከታወቀ መንግሰታዊ ባንክ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በCPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ መግዣ በሮቤ ከተማ አዶሼ ወለሼ ክፍለ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን ከሮቤ ከተማ አዶሺ ወለሼ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።
  5. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሰረት እውቅና የተሰጣቸውን እቃዎች የሚያቀርብ መሆን የኖርበታል።
  6. ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ፡የኮምፒውተር ቀለሞች ፣ቦርሳዎች ጨረታ ከመክፈቱ እንጂ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ማቅረብ አለበት።
  7. ለሰራተኞች ደንብ ልብስ የሚሆን ብትን ጨርቆች የተዘገጁ ልብሶችና የተለያዩ ቆዳ ጫማዎች ለከፋይ ምንጣፍና ለጨርቅ መጋረጃ እና ቀለሞች ናሙናዎች በሙሉ ለብቻ በፖስታ አሽገው ጨረታው ከመከፈቱ አንድ ቀን በፊት አስቀድሞ ውሉ ተፈጽሞ እቃው ገቢ እስከሚሆን ድረስ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የሚቆይ ናሙና እቃውን ማቅረብ አለባቸው።
  8. በሰነዶቻቸው ላይ ሥማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትከክል ጽፈው በመራረጥ እና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  9. የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
  10. በተገለጹት የእቃ ዝርዝሮች አጠገብ በተቀመጡት ባዶ ቦታዎች ላይ የእቃዎችን ብራንድና ሞዴል በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል።
  11. በሚጫረቱት ሰነድ ላይ ከተገለጸው ስፔስፍኬሽን ውጪ በመሰረዝና በመደለዝ የራስን ስፔስፍኬሽን መጨመር አይቻልም : አማራጭ ካላቸው ግን የሚወዳደሩበትን የእቃ አይነት በመጥቀስ ለብቻ በሌላ ወረቀት ማያየዝ ይችላሉ።
  12. ለሁሉም እቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  13. ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይቻልም።
  14. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
  15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታውን ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአገባቡ ሳይፈጸሙ ቢቀሩ ለውሉ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  16. የሚገዙ እቃዎች በተሰጠው ስፔስኬሽን መሰረት ተሟልተው ካልቀረቡና ኦሪጂናል ካልሆኑ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ  ከወጣበት ቀን አንስቶ  ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ተከፍቶ ውሉ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግዢ መመሪያ መሰረት የሚወሰን ይሆናል።
  18. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 12 18 35 27፣ ደውለው ይጠይቁ።

በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የአዶሼ ወለሼ ክ/ከ/ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ  ከወጣበት ቀን አንስቶ  ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 3፡30
  • Bid opening: 2026-09-10 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ  ከወጣበት ቀን አንስቶ  ለ15 የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በሮቤ ከተማ አስተዳደር የአዶሼ ወለሼ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T08:22:08.000Z
← Back to all tenders