Stationery

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የግዢ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የግዢ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት 1፣- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት፤ 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት - 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፣ ሎት 4- የደንብ ልብስ፣ ሎት 5፤- ፈርኒቸር ሎት 6- ኤሌክትሮኒክስ ሎት 7- የህትመት ውጤቶች፣ ሎት- 8 (ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ሎት፤- 9 ግማሽ ሊትር ውሃ ግዥ፣- ሎት 10፤- (የፎቶ ኮፒና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ)፣ ሎት 11- የመኪና ጌጣጌጥና መለዋወጫዎች እና ሎት 12 የሠራተኛ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ለተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማራችሁ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ የታከስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1፤- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ብር 4,000.00 ፣ ሎት - 2 የፅዳት ዕቃዎች ብር 5,000.00፣ ሎት፤- 3 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 5,000.00፣ ሎት 4- የደንብ ልብስ ብር 4,000.00፣ ሎት 5 ፈርኒቸር 5,000.00 ሎት 6 - ኤሌክትሮኒክስ 5,000.00 ሎት 7 - የህትመት ውጤቶች ብር 10,000.00፣ ሎት፤- 8 ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ ብር 3,000.00፣ ሎት – 9 ግማሽ ሊትር እሽግ ውሃ ግዥ ብር 5,000.00፣ ሎት 10 - የፎቶ ኮፒና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ ብር 3,000.00፣ ሎት 11 - የመኪና ጌጣጌጥና መለዋወጫዎች ብር 10,000.00 እና ሎት 12 የሠራተኛ የልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ብር 2,000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም አሠርተው ማቅረብ ሲኖርባቸው በጥቃቅን የተደራጁ ከአደራጃቸው የመንግስት መ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ በኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስም በማሠራት ማቅረብ አለባቸው!

3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መመሪያ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በመውሰድ የመወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮሚሽኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሜክሲኮ ስንጋ ተራ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሰነዱን ባስገቡበት ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ግዢ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ በዕለቱ ይከፈታል።

4. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ7 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት።

5. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን (የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ኦርጅናልና የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) በፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።

7. ወንበር ጠረጴዛና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ፣ ግማሽ ሊትር እሽግ ውሃ ግዥና የፎቶ ኮፒና ሌሎች የጥገና አገልግሎት ግዥ ለ በጀት ዓመት እንዳስፈላጊነቱ የሚቆይ

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም፣

9. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፤

10. በሰነዱ ላይ በተገለጸው ስፔስፊኬሽን እና ናሙና መሰረት በጨረታ ላሸነፉት ማቅረቢ የሚገባ ሲሆን ናሙና የሚያቀርቡበትም ዕቃ ከላስቲክ ውጭ ጠንካራ መሆን ይጠበቅበታል።

11. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፤

12. ማሳሰቢያ፡- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፤

የዋጋ ማቅረቢያውን በራስ ሞልቶ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም መሞላት ያለበት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የሚወዳደሩበትን ዕቃዎች ዋጋ ኮፒ ተደርጎ በመሙላት ብቻ ነው።

አድራሻ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ ሜከሲኮ ሠንጋ ተራ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ.011-557-7846 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Investment Commission
  • Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 09 ዮቤክ ኮሜርሽያል ሴንተር
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T08:33:48.000Z
← Back to all tenders