Stationery
የደጃች በቀለ ወያ ቅ/አንደኛና ተስፋ ኮከብ የመ/መ/ደረጃ ት/ቤት አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ት/ት ጽ/ቤት ስር የደጃች በቀለ ወያ ቅ/አንደኛና ተስፋ ኮከብ የመ/መ/ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- የጽዳት እቃዎች ፣
- የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ ቋሚ የቢሮ እቃዎች እና
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ እንዲሁም
- የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸሁና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስፕ የተመዘገባችሁ
- የዘመኑን ግብር የከፈላችሁና ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸሁ
- የቫት ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ
- በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ ለመስሪያ ቤቱ ስም የተጻፈ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበረያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለሎት 1 እና 2 ብር 5000/አምስት ሺህ ብር ለቀሩት ሎቶች ብር/3000/ ሦስት ሺህ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የእቃዎቹን ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በግልጽ ሞልተው ተስፋ ኮከብ የመጀመሪያና መካከስኛ ደረጃ ት/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒ አሽገው ማስገባት ደኖርባቸዋል።
ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 11ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
ማሳሰቢያ- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ት/ቤቱ የእቃዎቹን ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ከልደታ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት።
በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ት/ት ጽ/ቤት የደጃች በቀለ ወያ ቅአንደኛና ተስፋ ኮከብ የመ/መደረጃ ት/ቤት።
የደጃች በቀለ ወያ ቅ/አንደኛና ተስፋ ኮከብ
የመ/መ/ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dejach Bekele Weya Kindergarten & Tesfa Kokeb Elementary School
- Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ከልደታ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T08:58:11.000Z