Building Construction
የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ ሥራዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መለያ ቁጥር (EU-DDRR-014)
የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2019 በጀት –sf ሊያሰራ ላቀደው የቦና ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት ከሊኒክ ግንባታ ሥራዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1 ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ የሥራ ተቋራጮች 2019 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN N0 ) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ።
2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥረትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።
3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
4. የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ሕጋዊ (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትከክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
5 የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANIEL/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸው።
6. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተ.እ.ታ (VAT)፣ የተመዘገቡበትን ስርተፍኬትና ታከስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶከመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 ( ሃያ ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ፋይናንስ ክፍል በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
7. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ እና የሳይት ጉብኝት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
8 የጨረታው ሰንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦሪጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ፖስታ ላይ ስምና አድረሻ፣ የፕሮጀክቱን ስም፤ የተቋራጩን ስም እና ሰነዱ ኦሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን ለይቶ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 20 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዢ ፋይናንስ ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ይከፈታል።
10. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
11. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 212 4639 መደወል ይችላሉ።
በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-11
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
- Region: Sidama
- Publishing entity: የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T09:08:58.000Z