Materials

የእንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

የእንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም ፋ/ግ/ን/የስራ ሂደት በጨረታ ቁጥር 001 /2019 ዓ.ም መሰረት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለመማር ማስተማሩ የሚውሉ እቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ --

1 የጨረታው ሰነድ በየአንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር /200/ሁለት መቶ ብር ገንዘብ ቤት በመክፈል ከግዥ ክፍል ሰነድ መውሰድ ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው አካተው ማቅረብ ያለባቸው።

  • በዘርፍ የንግድ ፍቃድና በዘመኑ ስለመታደሱ የተረጋገጠ ማስረጃ
  • በወቅቱ የመንግስት ገቢ ግብር መክፈላቸውንና የቫት ተመዝጋቢ መሆናችውን ማረጋገጫ
  • በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ በአቅራቢነት የተመዘገቡ

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በፖስታ በማሸግ መወዳደር ይችላሉ።

4. የጨረታው ሳጥን ጨረታው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በት/ቤቱ /ፋ/ገን አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል።

5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ንብረት ክፍል ማቅረብ ይኖርበታል።

6. አሸናፊው ድርጅት ላሻነፈባቸው እቃዎች 20/100 ከውል በፊት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው።

7. ለሚያቀርቧቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

8. ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሲፒኦ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9 ጨረታውን አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ ጠቅለላ ዋጋ በመቶ/10% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዛዝ CPO ማስያዝ ይኖርበታ።

10. በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ።

  • ሎት1 ለአላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎች እና የአይነስውራን መርጃ መሳሪያ መፃፎች ዕቃዎች የላብላቶሪ እቃዎች ብር 15000
  • ሎት 2 የጽዳት እቃዎች -ብር 10,000
  • ሎት 3 የሰራተኞች የደንብ ልብስ--------ብር 10,000
  • ሎት 4 ቋሚ እቃዎች የቢሮ እና የልማት እቃዎች ----ብር 25,000
  • ሎት 5 የእስፖርት ትጥቅ እና መገልገያ እቃዎች----ብር 5000
  • ሎት 6 የድንብ ልብስና የመጋረጃ ስፊት ስራ ብር 5000
  • ሎት 7 የተለያዩ የህትመት ስራዎች -ብር 1000
  • ሎት 8 የኮንፒተር እና የፎቶኮፒ ማሽን ጥገናዎች------ብር 7000
  • ሎት 9 ተማሪዎችን እና የተለያዩ ሰራተኞችን መጓጓዣትራንስፖርት 3000

13. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ለጥቃቅን እና አነሰተኛ ተወዳዳሪዎች አምራች ድርጅት ካልሆናችሁ ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒዮ ማስያዝ ይኖርባችኋል ። የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት አይኖረውም።

በተጨማሪ ለበለጠ መረጃ -- እንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 31 ቁጥር ማዞሪያ ከፍ ብሎ ስልክ ቁጥር፡- 011 154 2102

በአዲስ አበባ ከተማ ት/ቢሮ በጉስሌ ክ/ከተማ ትም መምሪያ የእንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Entoto Amba Secondary School
  • Buyer address: እንጦጦ አምባ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 31 ቁጥር ማዞሪያ ከፍ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በእያንዳንዱ ሎት 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:26:04.000Z
← Back to all tenders