House and Building Sale

የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ የሆነ ቤት ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አቶ ኃይለማርያም ዓለም እና የፍ/ባለዕዳ አቶ እንዳለ ብዙነህ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/142983 3/11/2016ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/144389 በ10/11/2016ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ለገጣፎ ለገዳዲ ክ/ከተማ በካርታ ቁጥር L/XL/D/211882 የሆነውን በፍርድ ባለዕዳ ባለቤት በወ/ሮ ትዕግስት እሸቱ ፈለቀ ስም የተመዘገበ ቤት የሌለው ባዶ ይዞታ የቦታ ስፋት 250 ካ/ሜ ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 1,135,375 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ ሰባ አምስት) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ : ለመሸጥ ቀጠሮ ተይዞ በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.144389 በ21/11/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 283,843.75 (ሁለት መቶ ሰማንያ ሶስት ሺህ ስምንት መቶ አርባ ሶስት ከ75/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-09-28 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:37:45.000Z
← Back to all tenders