Stationery
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽዳት ዕቃዎ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብሶች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣ የህትመት አገልግሎት ግዥ፣ የካፌ አገልግሎት ግዥ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ እና የተለያዩ ዕቃዎች ክራይ አገልግሎት ግዥን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የሚያስፈልጋቸዉ።
- የጽዳት ዕቃዎች፤
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብሶች፤
- የደንብ ልብስ ስፌት፤
- ቋሚ ዕቃዎች፤
- መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፤
- የህትመት አገልግሎት ግዥ፤
- የካፌ አገልግሎት ግዥ፤
- ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ እና
- የተለያዩ ዕቃዎች ክራይ አገልግሎት ግዥን አጫርቶ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ መወዳደር የሚችሉ አቅራቢዎች፡-
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና TIN /የንግድ መለያ ቁጥር ያላቸዉ፤
- የሚፈለግባቸዉን ግብርና ታክሲ አጠናቀው መክፈላቸዉንና ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራብነት የተመዘገቡና ሰርተፍኬት ማቅረብ ሚችሉ ከአቅራቢነት ያልተወገዱ፤
- ቫት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በገቢዎች ቢሮ ተፈቀደ ደረሰኝ ሚጠቀሙ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናዉን እና ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ እና CPO በአንድ ላይ ማሸግ፣ ኮፒዎቹንም ለየብቻ ማሸግ እና የቴክኒካል ሰነድ ወይም ናሙና ለማቅረብ ለማያስፈልግ ለብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻ በትክከል በመሙላት 3ቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፤
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸዉ ከፍሎች በሙሉ በመሙላት እና የጨረታ ሰነዱ እና የዋጋ መሙያዉ ፎርም ሳይለወጥና ሳይቀነስ በሙሉ የማይመልስ ተጫራች ከጨረታዉ ይሰረዛል፤
- በበጥቃቅንና አነስተኛ፤ ነጋዴ ሴቶች ማህበራት እና አካል ጉዳተኛ መህበር የተደራጃቹ በራሳቹ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለምደረግ እና የጨረታ ሰነዱንም ያለ ከፍያ እንድትወስዱ፡- አምራች መሆናቹን፤ የመልካም ስራ አፈፀፀም ማስረጃ፤ ፈቃዳቹን ለሌላ ያላስተላለፋቹ መሆኑን የሚገልፅ፤ ወይም በአነስተኛ ብቻ ተደራጅቶ የቆዩ መሆኑን እና ሌሎች መረጃዎችን ከአደራጃዉ አካል የድጋፍ ደብዳቤ በጽ/ቤት ኀላፊ ብቻ የተፈረመ እና የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን የተጠቀሰበት ማቅረብ አለባቹ፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያዉኑ ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ላይ የሚከፈት ይሆናል። 11ኛዉ ቀን ስራ የለለበት ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይከፈታል፤
- ተጫራቾች ጨረታዉ ከመከፈቱ 2 ቀን በፊት ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ወይም ስፔስፍኬሽን ስለ ዕቃዉ በደንብ በሚገልጽ መልኩ ተዘጋጅቶ ማቅረብ መቻል አለባቸዉ፤ የናሙና መቀበያ ቅፅ በ2 ኮፒ አዘጋጅቶ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ አብሮ ማቅረብ መቻል አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ VAT ጨምሮ ያለ ስርዝ ድልዝ በትክክል መሞላት አለበት/ VAT/ የሌላቸዉ ያለ VAT ተብሎ መገለጽ አለበት/
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለዉ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም።
- በህዝብ ትራንስፖርት ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ከትራንስፖርትና ሎጂስትክ ባለ ስልጣን ፈቃድ ያለዉ መሆኑን መረጃ ማያያዝ አለባቸዉ፤ መረጃ ያላያያዘ ከጨረታዉ ይሰረዛል፤
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፤
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በያንዳንዱ ሎት በባንክ የተመሰከረለት CPO በሚያቀርቡት የገንዘብ ዋጋ።
|
ሎት |
የዕቃ / አገልግሎትዓይነት |
ከጠቅላላ ግዥ በ% |
የብር መጠን |
|
1 |
አላቂ ቢሮ ዕቃዎች |
0.75 |
31,000.00 |
|
2 |
ለጽዳት ዕቃዎች |
0.75 |
38,000.00 |
|
3 |
ቋሚ ዕቃዎች |
0.75 |
45,400.00 |
|
4 |
የደንብ ልብስ |
0.75 |
22,300.00 |
|
5 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
0.75 |
5,000.00 |
|
6 |
የህትመት አገልግሎት |
0.75 |
26,700.00 |
|
7 |
የመስተንግዶ አገልግሎት |
0.75 |
20,000.00 |
|
8 |
የተለያዩ ዕቃዎች ኪራይ አገልግሎት |
0.75 |
10,000.00 |
|
9 |
የካፌ አገልግሎት |
0.75 |
20,000.00 |
|
10 |
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አገልግሎት |
0.75 |
20,000.00 |
|
11 |
የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አገልግሎት |
0.75 |
2,000.00 |
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዉስጥ በወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) መግዛት እና እዛዉ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
አድራሻ፡- ከአዉቶቢስ ተራ ወደ አጣና ተራ በሚወስዳዉ መንገድ ሰፈረ ሰላም ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ
በአ/ከ/ክ/ከ ወረዳ 4 አስተዳደር አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 203 ነዉ።
ስልክቁጥር፡- 011-279-3338
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 10:15
- Bid opening (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ketema Sub City Woreda 4 Administration Finance Office
- Buyer address: ወደ አጣና ተራ በሚወስደው መንገድ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት 100 ሜትር ገባ ብሎ ሰፈረ ሰላም ት/ቤት ፊት ለፊት በአ/ከ/ክ/ከ/ ወረዳ 4 አስተዳደር ህንጻ ምድር ላይ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁ22
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T09:39:08.000Z