Stationery

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ መሣሪያዎች የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የህንፃ መሣሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የእንስሳት ህክምና መዳኒት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በ2019 የበጀት አመት ለማሰልጠኛ የሚሆኑ

  • መሣሪያዎች የፅህፈት መሳሪየዎች፤
  • የህንፃ መሣሪያዎች፤
  • የደንብ ልብስ፤
  • የእንስሳት ህክምና መዳኒት፤
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ - የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

  1. የዘርፉን ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የ2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
  2. በፌዴራል ወይም በክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የቲን ነምበር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል።
  4. ተጫራቾች ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ማካተት አለማካተታቸውን መግለጽ አለባቸው።
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት በጮሌ ቴ/ ሙት ስልጠና ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተጠቀሰው ቀናትና ቦታ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረተው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛኑ ዕለት ከሰዓቱ 8፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  8. ማንኛውም ተጫራች ካቀርበው ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በጮሌ ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ኮሌጅ ስም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በእጅ ማቅረብ ይኖርበታል።
  9. ተሸናፊ ተጫራች ለጨረታ ያስያዘውን ብር ወዲያውኑ ይመለስለታል።
  10.  አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ ወጪ ጮሌ ወረዳ ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ኮሌጅ ማቅረብ አለበት።
  11. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ - 09 27 23 84 92/ 09 32 13 45 9/ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡።

በአርሲ ዞን የጮሌ ወረዳ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-07 14:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Chole Woreda TVET college
  • Bid bond: 5000 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:57:42.000Z
← Back to all tenders