Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት የፅዳት እቃዎችን፣ የፅዳት አገልግሎትን፣ የህትመት አገልግሎትን፣ የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ (የአሻራ ማሽን) እና የተለያዩ የክሬን ኪራይ አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በግዥ መለያ ቁጥር፦ 002/2019 ለተቋማችን የስራ አገልግሎት የሚውሉ

  • የፅዳት እቃዎችን
  • የፅዳት አገልግሎትን
  • የህትመት አገልግሎትን
  • የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን እና
  • የተለያዩ የክሬን አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

/

የግዥ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

ሎት 1

የፅዳት እቃዎች ግዥ

50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር)

ሎት 2

የፅዳት አገልግሎት ግዥ

100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ሎት 3

የህትመት አገልግሎት ግዥ

30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)

ሎት 4

የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ (የአሻራ ማሽን)ግዥ

50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር)

ሎት 5

የክሬን ኪራይ አገልግሎት ግዥ

20,000 (ሀያ ሺህ ብር)

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No /ያላቸው
  5. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም የተዘጋጀ CPO ወይም የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ በተቀመጠው ሎት መሰረት ማስያዝ አለባቸው። ነገር ግን CPO ወይም የባንክ ጋራቲ በተቀመጠዉ ሎት መሰረት ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት በሪፖርተር ጋዜጣ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
  7. ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር1 እስከ 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት በእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ) በድርጅቱ ስም በተከፈት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000493811049 በመክፍል ያስገቡበትን ዲፖዚት ስሊፕ ይዘዉ በመምጣት ዘውትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ማሰልጠኛ አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት መግዛት ይችላሉ።
  8. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
  9. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒውን እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት አለባቸው፣
  10. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፣
  11. ጥቃቅንና አንስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸዉ ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ
    • ሀ.ከደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለበት
    • ለ. ሰነዱን በነጻ ለመዉሰድ በመመሪያ መሰረት ለምትወደደሩበት ዕቃ አምራች መሆን አለባቸሁ
  12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል።
  13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኝው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጷግሜ 3/2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከተጠቀሰው ሰዓት ዘግይቶ የመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  14. ጨረታው የሚከፈተው ጷግሜ 3/2018 ዓም ጠዋት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይሆናል።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት

ስልክ ቁጥር 011 470 8116

 


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Light Rail Transport Service Enterprise (AALRTSE)
  • Buyer address: Addis Ababa Light Rail Transit Service(Kality Depot) 1st Floor
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T14:20:27.000Z
← Back to all tenders