Building Construction
የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ ለዞኑ ጤና መምሪያ በክልሉ ጤና ቢሮ በ2019 በጀት አመት በጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳ ጤና ጣቢያዎች ቀሪ የግንባታ ስራ ለማጠናቀቅ በደቡብ ንጋት ጋዜጣ ጨረታ አሳውጆ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ ለዞኑ ጤና መምሪያ በክልሉ ጤና ቢሮ በ2019 በጀት አመት በጋሞ ዞን የተለያዩ ወረዳ ጤና ጣቢያዎች ቀሪ የግንባታ ስራ ለማጠናቀቅ
- ሎት 1) በጋርዳማርታ ወረዳ ጎጋሌ ጤና ጣቢያ
- ሎት-2) በጋጮ ባባ ወረዳ ዝጊቲ ባቆሌ ጤና ጣቢያ የፋርማስ ብሎክና ሴፍቲ ታንክ
- ሎት 3) በጨንቻ ወረዳ ዞዞ ጤና ጣቢያ የፋርማስ ብሎክና ሴፍቲ ታንክ
- ሎት-4) በቦረዳ ወረዳ ዘፋኖ ጤና ጣቢያ የፋርማስ ብሎክና ሴፍቲታንክ
በደቡብ ንጋት ጋዜጣ ጨረታ አሳውጆ ለማሰራት ይፈልጋል፡-
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸዉ BC/GC 8 ሆነዉ በበቃ አነስተኛ ደረጃ የተሸጋገሩ ኢንተርፕራይዝ ሆነዉ የሕጋዊነት መረጃ ከሚመለከተዉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ለ2019 በጀት አመት የተመዘገቡ ወይም የብቃት ማረጋገጫቸዉን ያሳደሱ እና እንዲሁም በሁሉም ሎት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸዉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸዉ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ለአቅራቢነት የተመዘገቡ።
- ማንኛዉም ተጫራቾች ከዉድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ነጠላ ዋጋ መሙላት እና ከየወረዳዉ ጤና ጣቢያ ሳይቱን ስለመመለከታቸዉ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች አስፈላጊዉን የግንባታ ዕቃ ፣ የሰዉሃይልና መሳሪያዎችን በራሳቸዉ ማቅረብ የምችሉ፡-
- አንድ ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ ማስገባት አይቻልም ከአንድ ሎት በላይ አስገብቶ የተገኘ ተጫራች ከሁሉም ዉድድር ወይም ጨረታ ዉጪ ይደረጋል።
- የጨረታ ማስከበሪያ(BID Security) ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200,000(ሁለት መቶ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናዉ የሂጋዊነት ሰነድ ዉስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሕጋዊ ፈቃዳቸዉንና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት በማቅረብ የጨረታዉን ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ እስከ 21(ሃያ አንደኛዉ) ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክን አድቫይስ ይዘዉ ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበዉ ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መዉሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፍ ከኮፒዉ በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት ፤ በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም ፣ አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንዲሁም፡- የህጋዊነት ሰነዶችን አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፍ ከኮፒ በተለያየ ፖስታ ከላይ በተገለጸዉ በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ እላዩ ላይ ማህተም ፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም አሽጎ እስከ 22ኛዉ ተከታታይ ቀናት 4፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጅዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘዉትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታዉ በ22ኛዉ (ሃያ ሁለተኛዉ) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
- ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታዉን መከፈት አያስተጓግልም።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁ 046-881-3338 ይደዉሉ።
የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛዉ ተከታታይ ቀናት 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-14 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛዉ ተከታታይ ቀናት 4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ
- Bid bond: 200,000 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Yedebub Nigat (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T16:15:57.000Z