Stationery
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አቅርቦቶችን ከሎት1-6 በተዘረዘረው መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 ኮምፒውተር፣ የኮምፒውተር መሳሪዎች እና ተጓዳኝ እቃዎች
- ሎት 3 የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች
- ሎት 4 የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች
- ሎት 5 የቢሮ እቃዎች ሎት
- ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው
2. የግብር ከፋይ መለያ ቲን/ ተመዝጋቢ የሆነ
3. የማወዳደሪያ ዋጋው ከብር 500000 (አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል።
6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች ሲፒኦ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 3% ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ማ/ም/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሰራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸውል።
8. ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት ይቻላል በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥኑ ይታሸግ እና በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀናት እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት መሰረት ጨረው ይታሸጋል፤ ጨረታውም ይከፈታል።
9. የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ማ/ም/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 መግዛት ይችላሉ።
10. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ወዲያውኑ ውል በመያዝ እቃውን በወረዳው በሚገኙ በየፑሉ ንብረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
11. ውድድሩ በጥቅል ድምር ወይም በነጠላ ሊሆን ይችላል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 622 0516/0006 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
በአብክመ በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን 4:30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Menze Mama Meder Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 3%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T07:10:29.000Z