Textile, Garments and Uniforms
በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የደንብ ልብሶች፣ የጽህፈት መሳረያዎች እና አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፤ የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች ላይ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Textile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather Products
Oromia
More tags
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureAmharic2merkatoGumbichu Woreda FEDB
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ሸዋ ዞን የጉ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ
- የደንብ ልብሶች፣
- የጽህፈት መሳረያዎች እና
- አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፤
- የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ፈርኒቸሮች፤
ላይ በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ተጋብዘዋል
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው ሆኖ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በፌዴራል ወይም በክልል ገንዘብ ቢሮ የአቅራቢዎች መዝገብ ዌብሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት ዌብሳይት ላይ መገኘታቸውን የሚያመላክት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 የደንብ ልብሶች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000(አስር ሺህ ብር) ብቻ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂና ቋሚ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ብቻ ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፤ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ- አምስት መቶ ብር) ብቻ ሎት 4 የተለያዩ የመኪና እቃዎች እና ጎማዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ብቻ ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ ሎት 6 ፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በብር ወይም CPO በማስያዝ መወዳደር የሚትችሉ ሲሆን እንዲሁም በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት በያንዳንዱ ሎት ከሚመለከተው አካል የጨረታ ማስከበሪያ ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርባችኃል፡፡በጨረታው የተሸነፉትም ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ በዋስትና ያስያዙት ብር ወይም CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15)ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ሸዋ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በተናጥል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተምም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት (15)ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ይሸጥና ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ሰነዱ መሸጥ ከጀመረበት ቀን ጀምሮ እስከ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ለጨረታው ሰነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በአስራ ስድስተኛው (16) የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡-ጉምቢቹ ወረዳ ጨፌ ዶንሳ ከተማ ከ አዲስ አበባ በሰንዳፋ በኩል 65 ኪ.ሜ ሲሆን በደብረ ዘይት 81ኪሜ
ስልክ፡- 0912230467ወይም 0911366403 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
የጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ (16) አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን እስከ 5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-10 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው (16) የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Gumbichu Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:00:22.000Z