Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ሙሉ በጀት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ሙሉ በጀት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • የተለያዩ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎችን፣
  • የተለያዩ አላቂ የጽዳት ዕቃዎችን፣
  • ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፣
  • ሞተር ሣይክል
  • የደንብ አልባሳትን የመኪና እና
  • የሞተር ሣይክል ጐማዎችን እና ከመነዳሪዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሰለሆነም ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ ዕቃዎቹ የሚገልጽ ሰነድ ዶክመንት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዶች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ም/ሸዋ ዞን የኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

የተጫራች ግዴታዎች

1.ከግዥው ጋር ተያያዥነት ያለውን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ በዚህም የሚጠበቅባቸውን የመንግስት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣ሕጋዊ የአቅራቢዎች ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የተጨማሪ እሴት ታከለ ወይም ቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ በኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ የሚችሉ እንድሁም ያሸነፉበትን ዕቃዎች ሳያደርጉ በፊት የዕቃዎቹን ናሙና ውሉን በወሰዱ 05 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይምችሉ፡፡

5. ተጨራቾች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በመሙላት ለድርጅቱ ኦርጅናል እና ኮፒ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም ስራ አፈጻጸም የሚውል ወይም የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው አቅርቦት 10% በሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨራቾች አሸናፍነታቸው በተገለጸላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርበው ውል መፈጸም ይጠበቅባቸዋል ።

7. አሸናፊ ድርጅት ባሸነፋቸው ዕቃዎች ያሸነፉበትን ዋጋ ከጨረታው በኋላ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ እስከ ሁለት (2) ወር መቆየት ይኖርበታል፡፡

8. ዕቃውን እስከ ወረዳው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

9. ከአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ውስጥ በተለያዩ ጥፋቶች ያልተሰረዙ ወይም የቅጣት ጊዜያቸው ያልተጠናቀቀ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡

10. ተጫራቾች ከነሐሴ 18/12/2018 ጀምሮ እስከ መስከረም 6/1/2019 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 3:30 ይከፈታል፡፡ ጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ በዚህ ቀን ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ኖኖ ወረዳ ግቢ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ተጫራቶች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን ሂደት አያስተጎጉልም።

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰብያ፤ ኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ 214 ኪ.ሜ ላይ የምሚትገኝ ሲሆን፤ በወልቂጤ መንገድ 216ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0912836006/ 0910154327 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

ኖኖ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-10 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Nono Woreda Finance and Economic Development Enterprise
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T08:29:29.000Z
← Back to all tenders