Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሣሪያ እና የቢሮ ፅዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጽሕፈት መሳሪያ ዕቃ ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ውሃ/ዕቃ/ግ/ጨ/ቁ-001/2019

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሣሪያ እና የቢሮ ፅዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  • በጽሕፈት መሣሪያ ዕቃ አቅራቢነት ዘርፍ የተሰማሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት፣ የቲን/TIN/ እና የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ዶክሜንት ሊገዙ ሲመጡ ኦርጅናሉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ አቅርበው እንዲመሳከር የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ/ ቢሮ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው አካውንት ቁጥር 1000454343507 ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይንም በሁኔታዎች ላይ ያልተገደበ ቢድ ቦንድ /unconditional Bid Bond/ ለ(90) የሥራ ቀናት የሚቆይ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ/ቢሮ ስም በማሠራት ከጨረታው ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማዘጋጀት አንድ (1) ኦርጅናልና ሁለት (2) ኮፒ በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ፖስታው ላይ ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ጽሑፍ ተለይተው መቅረብ አለበት፡፡
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በእያንዳንዱ የጽሕፈት መሳሪያ፣ የፅዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ ዓይነት በገዙት ኦሪጂናል ሰነድ ላይ ባለው ሰንጠረዥ ከነቫት በመጻፍ በሰም /በሙጫ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝ/ከል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ/ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታው ሳጥን በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ/ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  • የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል፡፡ በመክፈቻው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ያለመገኘት የጨረታ መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም::
  • አሸናፊ ተጫራች የጽሕፈት መሣሪያ፣ የፅዳትና ትናንሽ ኤሌክትሮኒክስ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝ/ክል/መ/ውሃ/ማዕ/ኢነ/ቢሮ ድረስ በማምጣትና ዕቃውን በማስፈተሽና የማስረከብ ግዴታ አለበት ፡፡
  • የዕቃ ናሙና ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት ከጨረታ ዶክሜንት ጋር ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል፡፡
  • ቢሮ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ 047 331 2551 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የውኃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ

ቦንጋ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T09:06:19.000Z
← Back to all tenders