House and Building Sale
የቦታ ስፋት 68.72 ካ.ሜ. የሆነ ኮንደሚኒየም ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አምሳለ ደምሴ እና የፍ/ባለዕዳ ዘላለም ተመስገን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/03 36636 በ18/04/2016ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/7347 በ23/04/2008ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቀድሞ በቦሌ ክ/ ከተማ በአሁኑ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስም መሪ ሎቄበሚባ አካባቢ ብሎክ 5 የቤት ቁጥር ML-BO5/NN410 የህንጻ መለያ ቁጥር AA00006100750205 የሆነ ኮንደሚኒየም ቤት የቦታ ስፋት 68.72 ካ.ሜ. የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 3,166,549 (ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አምስት መቶ አርባ ዘጠኝ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻስን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-30 14:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:09:24.000Z