Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ የተዘረዘሩት/ እቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3. የደንብ ልብስ
- ሎት 4 የላብራቶሪ ዕቃዎች እና የትምህርት መርጃ መሳሪያ
- ሎት 5. የተለያዩ አጋዥ መፅሐፍት እና አዳዲስ ልብ ወለዶች
- ሎት 6. የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች
- ሎት 7. የቢሮ ፈርኒቸር ጥገና እና የተለያዩ የኤሌክትሪክስ እቃዎች ጥገና
- ሎት 8. የህትመት ስራዎች
- ሎት 9. የህከምና ነከ እቃዎች
- ሎት10. መስተንግዶ
- ሎት 11. የመኪና ኪራይ ሲሆኑ
በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሳይደርስ ቤቴል በ40 ሜትር ቪክትሪ ት/ቤት ፊት ለፊት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 04 ቀርበው ሰነዱን መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
1. ተጫራቾች ከስራው ዘርፍ ጋር አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3.ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢዎች መሆን አለባቸው።
4. የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
5. ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ከገቢዎች ጊዜው ያላለፈ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
6. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ምዝገባ በኦንላይን የተመዘገበ መሆን አለበት።
7. በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስከበሪያ ፣ በውል ማስከበሪያ እና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትከ ተቋሙ ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ እንዲሁም የስምና የስራ ድርሻ ቲተር እና ክብ ማህተም ያሟላ የዋስትን ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል።
8. ተጫራቾች ጨረታው ሲከፈት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ CPO
- ሎት 1. 39,000 / ሰላሣ ዘጠኝ ሺህ ብር/
- ሎት 2. 19.900 / አስራ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር/
- ሎት 3. 20,000 / ሃያ ሺህ ብር/
- ሎት 4. 8,000 / ስምንት ሺህ ብር/
- ሎት 5. 8,000 / ስምንት ሺህ ብር/
- ሎት 6. 38,400 / ሰላሣ ስምንት ሺህ አራት መቶ ብር/
- ሎት 7. 9,400 / ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ብር/
- ሎት 8 8,000 /ስምንት ሺህ ብር/
- ሎት 9 5000 /አምስት ሺህ ብር/
- ሎት 10 10,000 /አስር ሺህ ብር /
- ሎት 11 10,520 /አስር ሺህ አምስት መቶ ሃያ ብር/ CPO /ሲፒአ / ከኦርጅናል ሰነዳችሁ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
በተጨማሪም ሲፒኦ CPO በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በፊንፊኔ ከተማ የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስም ማስያዝ ይኖራባቸዋል።
9. አሸናፊው ተጫራች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
10.ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን ሰነድ በትክክል በመሙላት ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
11. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12.ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል። እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
13. መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበውን ከውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% /ሃያ በመቶ/ መጨምር ወይም መቀነስ ይችላል።
14. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነድ ውስጥ የተካተተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 10 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ አሰርተው ውል መዋዋል አለባቸው።
15. ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል / ተመላሽ አይደረግም/
16. የእቃ ማስረከቢያ ቦታ በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ይሆናል።
17. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
18. ት/ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
19. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት በሂሳብ ከፍል ቢሮ ቁጥር 04 ውስጥ ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን የሚውል ከሆነ ቀኑን አሳልፈን የሚከፈት መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
20. የዕቃ ማጓጓዣ ብር አሸናፊው ተጫራች ይሸፍናል።
2..ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 07 የጄ/ዋ/ጉቱ 2ኛ ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ፡- 011 835 4110, 011 834 0970/ 011 835 4108
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: General Wako Gutu Secondary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:14:48.000Z