House and Building Sale
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ ነባር ቤቶችን መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ መለያ ቁጥር ፌቤ ኮ/ብ ግ.ጨ/አገ/15/12/2018
1. ለፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ስር የሚገኙ ነባር ቤቶችን በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/አገ/15/12/2018 መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውነው የቤቶች ሽያጭ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የመወዳደሪያ ተመን ዋጋ በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንኑ አስመልክቶ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መመሪያ መሰረት ነው፡፡
4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ነሃሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም አስከ መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ 2፡00 እስከ 11፡00 ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በካሽ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድን ለገሐር በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት በሚገኘው ዋና የመሰብሰቢ ኣደራሽ 1ኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መስከረም 2 እና መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ እንዲመልሱ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ሲፒኦ በፌዴራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ክፍል 1 ላይ በተገለፀበት ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ቤቶቹን በአካል ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ማብቂያው ቀን ድረስ በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ቤቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ድረስ በመቅረብና ለዚሁ ስራ በሚመደቡ ባለሙያዎች እና በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ቤቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 011-8-55-36-12 ወይም 011-8-55-36-17
0911-80-92-63 ወይም 0913-35-6232 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ዌብሳይት website www.fhc.gov.et
የፖ.ሣ.ቁ. PO, Box 299
ፋክስ ቁጥር፡ 011-5-54-60-45 / 011-5-52-46-46
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-13
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): መስከረም 2 እና መስከረም 3 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ
- Bid opening: 2026-09-13 17:30
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Housing Corporation
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:15:04.000Z
- Buyer website: https://www.fhc.gov.et