House, Building and Warehouse
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኝ ለጋራዥ አገልግሎት እስከነቢሮው የሚውል ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የጋራዥ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር- -RE-EMC/OT /GARAGE RENT/01/2019
የኢትዮጵያ ማዕድን፣ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኝ ለጋራዥ አገልግሎት እስከነቢሮው የሚውል ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት
|
ብዛት |
ጠቅላላ ስፋት
|
የጨረታው መዝጊያ |
የጨረታው መክፈቻ |
ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ቀን |
|||||
|
|
ለጋራዥ አገልግሎት የሚውል ቦታ እስከነ ቢሮው |
1 |
1093.65m2
|
04/13/2018ዓ.ም
|
4:00ጠዋት
|
04/13/2018 ዓ.ም |
4:30 ጠዋት
|
እ.አ ዋናው መስሪያ ቤት
|
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች) ፡-
1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኪራይ በዘርፉ ለ2018በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታከስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ 2 በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሶፍት ኮፒ(soft copy) መውሰድ ይችላሉ፣
2. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጀውን ጋራዥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመከፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ጋራዡ በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል፡፡
3. ተጫራቾች ለሚከራየው ጋራዥ የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20 %(ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ህጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
4. የጨረታ አሸናፊው ጋራዥ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡ ውሉ ለሁለት አመት የሚቆይ ይሆናል፡፡
5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ የግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈም ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ለሚከራዩት ጋራዥ ስፋት ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት በግልጽ ሞልተው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡ ፡ ተጫራጮች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
10 ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ +251-0911622263
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-09 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
- Buyer address: 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:24:35.000Z