Stationery

የጎባ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጎባ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማው ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ

  • የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
  • ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
  • ፈርኒቸሮች፣
  • የሕንጻ መሣሪያዎችን፣
  • የተለያዩ ዕቃዎች፣
  • የተለያዩ ሕትመቶችን፣
  • ምግብ እና ምግብ ነክ አገልግሎቶችን እና
  • ለቴክኒከ እና ሙያ ሥልጠና አገልግሎት የሚውሉ መሣሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን። ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን ይሆናል። በ11ኛው ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  3. በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ መስፈርት መሠረት እውቅና የተሰጣቸውን ዕቃዎች የሚያቀርብ መሆን ይኖርበታል። እንዲሁም ኤሌክትሮኒክሶችን በተመለከተ ናሙና እና ፎቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረምና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
  5. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
  6. ተጫራቾች በተገለፀው ዕቃ ዝርዝሮች አጠገብ በተቀመጡት ባዶ ቦታዎች ላይ የዕቃዎቹን ብራንድና ሞዴል በመሙላት መወዳደር ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይጠቀስ ቀርቶ የመወዳደሪያ ዋጋ ብቻ ያቀረበ ተወዳዳሪ በተሻለ ብራንድና ሞዴል ተጠቅሶ እንደቀረበ ተደርጎ ይወሰዳል።
  7. ተጫራቾች በሚጫረቱት ሰነድ ላይ ከተገለጸው ስፔስፊኬሽን ውጭ በመሰረዝ እና በመደለዝ የራስን ስፔስፊኬሽን መጨመር አይችሉም። አማራጭ ካላቸው ግን የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት በመጥቀስ ለብቻ በሌላ ወረቀት ማያያዝ ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
  9. አቅራቢው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማንኛውንም ወጪ በመቻል መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
  10. አቅራቢው ድርጅት ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ 50,000 (ሐምሳ ሺ) ብር ለግዥ አገልግሎት እና ለአገልግሎት 20,000.00 (ሐያ ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርበታል።
  11. አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ የያዘውን ብር ለመንግስት ገቢ በማድረግ ወደ ሚቀጥለው ርምጃ ለማለፍ የሚገደድ ይሆናል።
  12. አሸናፊዎች ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  13. ለውል ማስከበሪያ በዋስትና ሰነድ የተያዘው በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ውሉ መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ተይዞ ይቆያል።
  14. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች የጨረታውን ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ማስከበሪያ በዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
  15. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ኦሪጂናል ካልሆኑ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  16. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ በግዢ መመሪያው መሠረት የሚወሰን ይሆናል።
  17. መ/ቤቱ ለአቅራቢው/ለነጋዴው ከፍያ የሚፈጽመው ለማቅረብ ውል የፈረመባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ጥራታቸውን ጠብቀው በንብረት ክፍላችን ገቢ መሆናቸው ሲረጋገጥ ይሆናል።
  18. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙለ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በሮቤ ከተማ አስተዳደር  የጎባ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀን
  • Bid opening: 2026-09-05 17:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: ጎባ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T09:36:26.000Z
← Back to all tenders