Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በቢሾፍቱ ከተማ የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በቢሾፍቱ ከተማ የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት አገልግሎት የሚዉሉ

  • ልዩ ልዩ ለቢሮ ዉስጥ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎችን፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮንክስና ፈርኒቸሮች፣
  • የተለያዩ የመኪና ጎማ፣ የደንብ ልብስ እና
  • የተለያዩ የህትመት ሥራዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸዉን መመሪያ በመከተል ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው -ገጽ እስፔስፊኬሽን መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑ ግብር የከፈሉና ያሳደሱ መሆን ይኖርባቸዋል

2. ተጫራቾች ከ100,000.00 ብር በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸዉ ፈቃድ ሰጪ አከላት አቅራብዎች ዝርዝር  ተርታ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

4. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከሆኑ ከገቢዎች ወይም ከጉሙሩክ በየሦስት ወር የተጨማሪ እሴት ታከስ መክፈላቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡

5. ማንኛዉም ተጫራቾች በጨረታዉ ተካፈይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ካቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ከህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከ2፡30-11፡30 ሰዓት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በጨለለቃ ክፍለ ከተማገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር- ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቸቶች በጨረታ በስነዶቻቸዉ ላይ አድራሻዉን ስልክ፤ ፖሰታ ፣እሜል ፣የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በትክክል መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

8. መ/ቤቱ ካቀረበዉ እስፐሲፊኬሽን ወይም መስፈርት /Standard / በታች ማቅረብ አይቻልም ።ሰነዱን መሰረዝ መደለዝ አይቻልም፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖሰታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራች ወይም ድርጅት ያሸነፈዉን ዕቃ በራሱ ትራንስፖሪት ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋዘን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

11. ማንኛዉም ተጫራቾች ጨረታዉ ከተከፈተ በኃላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛዉንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታዉን ትቼዋለሁ ማለት አይቻልም።

12. ጨረታዉ የሚቆየዉ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡ በነጋታዉ በ15ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸሁ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸሁ የማይገኙ ከሆነ ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል ። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

13. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

14. በተጨማሪም ሙሉዉን መመሪያ ከሚገዙት ሰነድ ጋር ስላለ ሰነዱን ሲገዙ የሚያገኙ ይሆናል፡፡

አድራሻ- ቢሾፍቱ ከተማ ኦዳ ነቤ ሆቴል ፊት ስፌት 100 ሜትር ገባ ብሎ ማግኘት ይቻላል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114342001/0923008007ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

ቢሾፍቱ ከተማ የጨለለቃ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታዉ የሚቆየዉ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡ በነጋታዉ በ15ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-10 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታዉ የሚቆየዉ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡ በነጋታዉ በ15ኛዉ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Cheleleka Sub City Woreda Court
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T11:22:19.000Z
← Back to all tenders