Stationery
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በክ/ከተማ አስተዳደር ለሚገኙት መንግስት መ/ቤቶችና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በክ/ከተማ አስተዳደር ለሚገኙት መንግስት መ/ቤቶችና ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ።
- በሎት 1፡- የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የንጽህና መሳሪያዎችን፣ ቋሚ አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን፣ የሠራተኛ የደንብ ልብሶችን፣ የተለያዩ ቀለሞችን፣
- በሎት 2፡- የኤሌክትሮኒክስ፤ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችንና የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዘርፉ ህጋዊ ታደሰ የንግድ ፍቃዱ ያለውና በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟለው የንግድ ድርጅት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 1,000 ብር (አንድ ሽህ ብር ብቻ) ወደ ሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1064669901216 ገቢ በማድረግ (በመክፈል) ደረሰኙን በመያዝ ከፉሪ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ።
2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ ከባንክ የተረጋገጠ CPO 150,000.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ሽህ ብር ብቻ) በፉሪ ክ/ከተማ ንዘብ ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከሠነድ ጋር በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል (የሲንቄ ባንክ CPO ቢሆን ይመረጣል)።
3. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ስምና አድራሻ በማድረግ በድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ማህተምና ፊርማ በማረጋገጥ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በፉሪ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02 ማስገባት አለበት።
4. ተጫራቾች የተጨማሪእሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር ሆኖ እቃዎቹ ጥራቱን የጠበቁ መሆን ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ሊያቀርቡት ዋጋ ያሉትን 1 እቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበቸዋል።
9. የጨረታው በማስታወቂያጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል። እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
10. ግዥ ፈፃሚ መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ፉሪ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 48 93 72፤ 09 38 17 36 74 ደውለው መጠየት ይቻላል።
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ አስተዳደር የፉሪ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-10 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City Administration, Furi Sub-City Finance Office
- Bid bond: 150,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:00:25.000Z