Textile, Garment and Leather
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያዎችን ፡ የጽዳት እቃዎችን ፡ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፡ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የጽህፈት መሣሪያዎችን ፡ የጽዳት እቃዎችን ፡ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎችን፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፡ የተለያዩ የመኪና ጎማዎችን እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
1- በዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው 2018/2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ና የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ገንዘብ ሚኒስቴር በወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
2- አሸናፊ ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአሥር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች በሙሉ ኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል
3- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ድረስ ብቻ የማይመለስ ብር 1000 ብር ( አንድ ሺህ ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000036504416 በመክፈል ስሊፕ ለኩዩ ወረዳ ገቢዎች ቢሮ በማስገባት በማወራረድ ሰነዱን ከኩዩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መውሰድ ይችላሉ፡፡
4- ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃ የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ ሰነድ በፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ) CPO በባንክ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለበት ፡፡ ማስከበሪያውን ካላስገባ (ካለስያዘ) ፖስታው አይከፈትም፡፡
5- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጫረታውን ከመከፈት አያግደውም
6- በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
7- ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የሥራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል፡፡
8- መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፤
9- በ2018 ዓ/ም በጽ/ቤታችን ተወዳድራችሁ ከአሸነፋቹ በኋላ ያሸነፋቹትን ዕቃዎችን ስምምነት በመግባት እንዲታቀርቡ ቢነገረችሁም ፍቃደኛ ያልሆናችሁና ያላቀረባችሁ ዘንድሮ የማናስተናግዳችሁና የማናወዳድራችሁ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
10- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0935 971 038 / 0911 775 600 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-09 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: North Shewa Zone Kuyu Woreda F/E/D/B
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:21:27.000Z