Textile, Garment and Leather
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ለሚ/ኩ/ክ/ከ/ወ/14/ፋ/ 563/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም፡-
ሎት1. የደንብ ልብስ ሎት2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት3. የፅዳት ዕቃዎች ሎት4, የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ሎት5. ልዩ ልዩ የቢሮ እቃዎች ሎት6. የመኪና ጎማ ግዥ ሎት7. መስተንግዶና ካፌ አገልግሎት ሎት 8. የትራንስፖረት አገልግሎት ኪራይ ሎት9. የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች ሎት 10. የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ ሎት11. የኪራይ እቃዎች ሎት12. ህትመት ስራዎችን ሎት 13. የግብርና ግብዓቶች ሎት 14. ለምገባ ሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና የልጆች መጫወቻዎች የፈርኒቸር ጥገና ሎት 15. በመጀመሪያ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
ተወዳዳሪ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው (TIN NUMBER)
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የካ አባዶ ገደራ ገዛህኝ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውን እና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በወረዳው ፋ/ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡
5. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ለይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
6. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈውን ዕቃ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ የግዥ ቡድን በአካል ቀርበው ውል መግባት አለባቸው፡፡ አሸናፊው ውል ሳይዙ ዕቃ ጭነው ቢመጡ ወደ መጋዝን ማስገባት አይችሉም፡፡
7. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊውና ለተሸናፊ በእኩል ጊዜ በፅሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንገልፃለን፡፡
8. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጁ በስልክ ቁጥር 011-86-60 491 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
አድራሻ፦ የካ አባዶ ገደራ ገዛኸኝ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ይገኛል።
011 893 18 25
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በለሚ ኩራ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-05 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lemi Kura Woreda 14 FEDB
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:35:05.000Z