Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል።

የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ

  • ሎት 1 የጽሕፈት ዕቃዎች 16000
  • ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 23000
  • ሎት 3 የፅዳት ዕቃዎች 10000
  • ሎት 4 መድሀኒቶች እና የህክምና ዕቃዎች የሚወገዱ መድሀኒቶች 25000
  • ሎት 5 የደንብ ልብስ 15000
  • ሱት 6 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 20000
  • ሎት 7 ልዩ ልዩ ዕቃዎች 2500
  • ሎት 8 የጥገና ስራዎች የውሃና መብራት ጥገና የኮምፒውተርና ፕሪንተር ጥገና 15000
  • ሎት 9 የ4k መኪና ጥገና እና ሰርቪስ 2000 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች (አቅራቢዎች) በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋበዛለን።

1. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ህጋዊ የሆነ፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውንና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል። ለዚህም የሰነድ ማረጋገጫ ኮፒ እና ዋናውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀረቧቸውን እቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ባሉት ቀናት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። እንዲሁም ቋሚ እና የህክምና ዕቃዎች በተመለከተ በካታሎግ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።

3. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተጫራቾችመሳተፍ ይችላሉ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለማግኘት የሚችሉት ከተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ተገቢና የተሟላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ ማስገባት ይኖርበታል።

5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፤ ህክምና ላይ የምትወዳደሩ አቅራቢዎች የምታቀርቡት መድሃኒትና ሬጀንቶች የአገልግሎት ዘመናቸው 2 አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።

6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ የአንድ ሎት ዋጋ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

7. አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት።

8. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 43 ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ማስገባት አለባችሁ።

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት በጤና ጣቢያው የስብሰባ አዳራሽ አራተኛ ፎቅ ቁጥር 44 ይከፈታል።

10. ተቋሙ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሟሟላት የሚችሉ አቅራቢዎች የጨረታውን ሰነድ ዘነበወርቅ ወይም ከአለርት ሆስፒታል 300 ሜትር ገባ ብሎ ልዩ ሰሙ ቆሼ የሚባል አካባቢ ሲሆን በዚሁ ኮ/ቀ/ክ/ከ ወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ፋይናንስ እና ግዥ ክፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 43 መጥቶ መግዛት ይችላሉ።

አድራሻ፡-- ከአለርት ሆስፒታል ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011 369 8915 ይደውሉ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-09-05 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keranio Sub City Administration Health Office Woreda 01 Health Center
  • Buyer address: ከአለርት ሆስፒታል ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ከአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን 100 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T13:14:58.000Z
← Back to all tenders