Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሜይዴይ ቅደመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት የበጀት አመቱ በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Cleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationeryOffice Supplies and Services
Addis Ababa
More tags
Sport Materials and EquipmentTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsTextile, Garments and UniformsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOthersMaintenance and RepairOffice Machines and ComputersHealth Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and SuppliesPharmaceutical ProductsPrinting and PublishingCatering and Cafeteria ServicesFood Items and DrinksFood and BeveragePrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionAmharic2merkatoMayday Elementary School
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሜ 002/2019 ዓ.ም
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሜይዴይ ቅደመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት የበጀት አመቱ በግልጽ ጨረታ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች
- የደንብ ልብስና የአስፖርት ትጥቅ እቃዎች
- የተለያዩ አላቂ የፅዳት እቃዎች
- የኤሌትሮኒክስ እቃዎች
- አላቂ የህክምና እቃዎች
- የኮምፒዩተር፤ የፕሪንተርና የኮፒ ማሽን ጥገና
- አላቂ የህክምና እቃዎች
- የህትመት ስራዎች
- የተለያዩ የጥገና ስራዎች
- የመስተንግዶ ስራዎች ኩኪስ፤ ውሃና ቆሎ
- የመምህራንና የአሰራተኞች የሻይ ቤት የመስተንግዶ ክበብ
- የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 4000.00 ብር
- ሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 6000.00 ብር
- ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 4 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሉት 5 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 6 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 7000.00 ብር
- ሎት 7 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 8 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 9 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት ıo የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 1 የጨረታ ማስከበሪያ (1%) 3000.00 ብር
- ሎት 12 የጨረታ ማስከበሪያ 1(%) 4000.00 ብር
በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው የግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ያለው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ ከ 3 ቀን በፊት ናሙናውን በዝርዝር ማቅረብ አለባቸው። በናሙና (ሳንፕል) ማቅረብ የማይቻል ቋሚ እቃ በከለር ፎቶ ማቅረብ አለበት። በተጨማሪም የት/ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ቦታው ድረስ በመሄድ እቃው ያያል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ አለባቸው። ጨረታውን የሚያቀርበውና የሚፈፅመው ወኪል ከሆነ ከፍ/ቤት የተሰጠውን ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላሉ። ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ሲመልሱ ሰነዱ ላይ እያንዳንዱ ገፅ ላይ ማህተምና ፊርማ በእርሶ በኩል መሞላት ያለበት ተሞልቶ መመለስ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና በምንሰጣቸው የዋጋ ቅፅ መሆን አለበት ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ዋናውንና ኮፒውን
- የመወዳደሪያ ዶክመንት በታሸገ በ4 (አራት) ፖስታ በት/ቤቱ ፋይናስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10ኛው የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባችዋል። ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ ብር 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከተከፈተ በውኃላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ራሳቸው በሚያመርቱት ምርት መሆን አለበት ካደራጃቸው ወረዳ የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ ደብዳቤ (CPO) እና የውል ማስከበርያ 10% በተጨማሪም ያፀደቀላው አካል ህጋዊ ማንነት በመግለጽ መወዳደር እንዲችሉ እየገለፅን ሰነዱን በመውሰድ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የእቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለፅ የሰነድን ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የሜይዴይ ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ የመ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Bid opening: 2026-09-05 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Mayday Elementary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T13:18:56.000Z