Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በኦሮሚያ ክልል በጂማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ በ2019 ዓ.ም የበጀት ዘመን ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- የጽሕፈት እና የጽዳት ዕቃዎች፤
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
- ቋሚ ዕቃዎች /ፈርኒቸር/ ፣
- የግንባታ ዕቃዎችን፤
- የመኪና እና ሞተርሳይክል ጎማ እና መለዋወጫ ዕቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጥገና ሥራዎች
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተለውን መስፈርቶች ማማላት ይጠበቅባቸዋል
1. ከላይ በተጠቀሱት የአቅርቦት ዘርፎች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው።
2. ማንኛውም የሀገር ውስጥ ተጫራች ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዝገቡ መሆን አለባቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ፤ ቲን ነምበር እና የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለተጫራቾች ለእያንዳንዱ አቅርቦት ዘርፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000 (ስድስት ሽህ) ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /CPO/ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅበታል፤ በተጨማሪም አሸናፊው በ15 ቀን ውስጥ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በባንክበ ተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ አቅርቦ አስይዞ ውል መፈረም ግዴታ አለበት።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ፎቶ ኮፒ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከቀርሳ ወረዳ ከገቢዎችና ጉምሩክ በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ) ብር በመክፈል ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ የወረዳው ገንዘብ ቢሮ ቁጥር 2 እስከ 11፡00 ሰዓት መግዛት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በ16ኛ ቀን እስከ 6፡00 ገብቶ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ በ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ሰነዱ የተሟላ ከሆነ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጎልም። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
6. አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ ማንኛውንም ወጪ ችሎ ቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ እስቶር (ንብረት ክፍል) ማቅረብ ግዴታ አለበት።
7. የጨረታው ሰነድ ከተከፈተ ቀን አንስቶ ለ6ዐ /ስልሣ/ ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
8. ተጫራቾች ተጨማሪ መስፈርቶችን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
9. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ላይ ስም፣ ፊርማ፣ አድራሻ፣ ክብ ማህተም እና ስልክ ቁጥር ሊኖረው ይገባል።
10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
11. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 113 0478 / 047 113 0011/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
በጅማ ዞን የቀርሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ሰርቦ
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን እስከ 6፡00
- Bid opening: 2026-09-10 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን እስከ 8፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Kersa Woreda FEDB
- Bid bond: 6000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T13:22:39.000Z