Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • አላቂና ቋሚ እቃዎች የጽህፈት መሳሪያ፣
  • የመኪና ጎማ ፣
  • የመኪና መለዋወጫ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና
  • የጽዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
  • ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሱ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. ከሚያቀርቡት ከሚወዳደሩበት አታ ጋር የተዛመደ፣ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።

3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ እንዲሁም ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎቹ ግን የገንዘብ መጠን ሳይኖረው ማንኛውም ተጫራች የተጨማሪ እሴት ታስክ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ያገኙታል፤

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/አስ/ርደ/ስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ማግኘት ይቻላል፤

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ)ወይንም ጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ኮፒ ማስያዝ አለባቸው፣

8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዘት የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰ/ከ/አስ/ር ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙ በሰ/ከ/አስ/ር/ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በግልፅ ይከፈታል፣

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

10. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊ ከሆነ የጨረታውን ውል ማስከበሪያ ያቀረቡትን የጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የመንግስት ስራ ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ጊዜ እና ሰዓት ይከፈታል።

12.ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዕቃ ውድድሩ በሎት/በጠቅላላ ድምር ስለሆነ የሚሞሉት የጨረታ ሰነድ አንዱም ዕቃ ሳይሞሉ ከቀሩ ከጨረታው ውድድሩ ውድቅ ይሆናሉ።

13. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፋቸውን እቃዎች ቦታው ድረስ ማለትም ሰ/ከ/አስ/ር ገንዘቡ ጽ/ቤት ድረስ በማምጣት አስረክቦ ሂሳቡን እራሱ ማወራረድ ይኖርበታል።

14. በባለሙያ መታየት ያለባቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ባስቀመጠው ባለሙያ መሰረት ጥራታቸው ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል።

15. ተጫራቾች ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በሰ/ከ/አስ/ር ግ/ፋ/ን/አስ/ር/ደ/የስ/ሂደት

ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 1040/41 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የሰቆጣ ከተማ አስ/ር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-09 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Sekota City Administration Finance Office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T13:51:32.000Z
← Back to all tenders