Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ትምህርት ጽ/ቤት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ትምህርት ጽ/ቤት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  • ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ
  • ሎት 4 የህትመት ስራዎች
  • ሎት 5 አላቂ የህክምና እቃዎች ፣ የላብራቶሪ እቃዎች
  • ሎት 6 የትራንስፖርት እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማሶገድ ስራዎች
  • ሎት-7 የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች
  • ሎት 8 የውሃ እና ቆሎ አቅርቦት
  • ሎት 9 ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች
  • ሎት 10 የኮምፒውተር፣ ፎቶ ኮፒ፣ ማባዣ፣ ጥገና
  • ሎት 11 የዲስክ ብየዳ፣ ቀለም ቅብ ስራ የተማሪዎች በር ብየዳ ስቶር ቤት ስራ

ከላይ በተዘረዘሩት ሎቶች መሰረት ፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN no ያላቸው

4. ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ

5. ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የሚያመርቱት ምርት ተጠቅሶ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣

6. የአቅራቢነታቸው ከዌብሳይት ላይ ሲረጋገጥ ተመዝግቦ መገኘት የሚችል ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቀኑ 2፡30-11፡30 ሠዓት ድረስ የማይመለስ 300.00 ብር/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በሰንጠረዡ ሥር በተቀመጠው ዝርዝር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፤ ተወዳዳሪዎች ማስረጃቸውንና የእቃዎቹን በአራት ኢንቭሎፕ ማለትም ፋይናንሻል ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ኮፒ(ቅጂ)፣ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ቴክኒካል ኮፒ (ቅጂ) ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

ሎት

የእቃው /የስራው/ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን

የአጠቃላይ በጀቱ የተወሰደው ብዜት

1

አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች

4000

0.5

2

የጽዳትዕቃዎች

4000

0.5

3

የደንብ ልብስ

10,000

0.5

4

የህትመት ስራዎች

4000

0.5

5

አላቂ የህክምና እቃዎች ፣ የላብራቶሪ እቃዎች

4000

0.5

6

የትራንስፖርት እና ፍሳሽ ቆሻሻ ማሶገድ ስራዎች

4000

0.5

7

የተለያዩ ለጥገና የሚውሉ እቃዎች

4000

0.5

8

የውሀ እና ቆሎ አቅርቦት

3000

0.5

9

ቋሚ መገልገያ እቃዎች እና መሣሪያዎች

8000

0.5

10

የኮምፒውተር፣ ፎቶ ኮፒ፣ ማባዣ፣ ጥገና

1500

0.5

11

የዴስከ ብየዳ፣ ቀለም ቅብ ስራ የተማሪዎች በር ብየዳ ስቶር ቤት እና የዶሮ ቤት ስራ

17,500

0.5

7. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ /specification/ ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም።

8. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ (CPO) 10% ያሲዛሉ።

9. የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን አብቅቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ሠዓት በት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገርግን የሚከፈትበት ካላንደር የሚዘጋው ቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሀገር አቀፍ ከብረ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

10. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ሎቶች ላይ ናሙናዎችን በማዳበሪያ አድርጎ ከጨረታው ማብቂያ የመጨረሻ ቀን አንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው። ለናሙና መረካከቢያ የሚቀርበው ፎርም ድርጅቱን የሚገልፅ እና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል ።

11. የጨረታ አሸናፊ ድረጅት ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብና የማስረከብ ግዴታ አለበት።

12. ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ፌታ/ሀ/ጊ የመ/ደ/ት/ቤት ጥቁር አባይ ጫማ ፋብሪካ ወረድ ብሎ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ ስ/ቁጥር 011-273-0565 ወይም 011-270-1787 ፣ 09-13-96-26-44

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት ፅ/ቤት የወረዳ 14 ፊታ/ሀ/ጊ/ቁ.1 የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን አብቅቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-09-07 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን በ10ኛው ቀን አብቅቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Fitaurari Habte Giorgis Primary School
  • Buyer address: አስኮ ከጥቁር አባይ ጫማ ፋብሪካ ወረድ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T14:17:46.000Z
← Back to all tenders