Stationery

በጂማ ዞን የስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በጂማ ዞን የስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት የጽህፈት መሳሪያ፣የጽዳት እቃዎች፣ፈርኒቸሮች፣ኤሌክትሮኒክስ የደንብ ልብስ፣ አጠቃላይ የግንባታ እቃዎች፣ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ሞተር ሳይክሎች፣ ጎማዎች፣ የመኪኖች እና ሞተር ብስክሌቶች መለዋወጫ መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ አይነት ዘሮች፣ የተለያዩ የህትመት እና የጥገና አገልግሎቶች፣ የጭነት አገልግሎት፣ የእንጨት እና የብረታብረቶች ስራ አገልግሎት፣ የተዘጋጀ የምግብ ና የመጠጥ አቅርቦት አገልግሎት ከህጋዊ የንግድ ተቋማት አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እጩዎች ማመልከት ይችላሉ።

1. አዲስ ወይም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ይህንን ተግባር በቀጥታ የሚገልጽ።

2. ቲን Number ቫት እና በQRኮድ የታተመ ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ የሚችል።

3. ግብር መክፈላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከገቢዎች ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።

4, በመንግስት ግዥ አቅርቦት ውስጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር) ማቅረብ የሚችል።

6. በማህበሩ የተደራጁ እጩዎች የማህበሩን ህጋዊ አካል የሚገልጹ አዲስ ወይም የታደሱ ሰነዶች ሊኖራቸው ይገባል።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀን 21/ /12/2018 እስከ 05/01/2019 ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8. አሸናፊው ጨረታው በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ ከስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጋር ይፈርማል።

9. የጨረታው አሸናፊ እቃውን እስከ ስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት።

10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 05/01/2019 ድረስ የጨረታ ሰነዱን በማሸግ በስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ክፍል 2 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ በፖስታ ታሽጎ ከድርጅቱ ማህተም፣ አድራሻ፣ ስም እና ፊርማ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቀን 05/01/2019 በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 05/01/2019 በ5፡30 ሰዓት ይከፈታል።

13. ጽህፈት ቤቱ ሌሎች አማራጮች ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ለበለጠ መረጃ፡- 09 17 01 93 37፣ 09 12 10 94 50፣ 09 89 03 80 40 ይደውሉ
በጂማ ዞን የስግሞ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-09-15 11:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jimma Zone Sigimo Wereda FEDB
  • Bid bond: 30,000 (ሰላሳ ሺ ብር)
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
  • Posted at: 2026-08-27T08:04:55.000Z
← Back to all tenders