Materials
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2019
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን መግዛት ስለሚፈልግ በወጣው ግልፅ ጨረታ ላይ ተመስርቶ በተዘጋጀው ጨረታ መሰረት
- ሎት አንድ አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣
- ሎት ሁለት የደንብ ልብስ፣
- ሎት ሦስት አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት አራት ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት አምስት የኤሌክትሮኒክስ አላቂ እና ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት ስድስት የህትመት ስራዎች፣
- ሎት ሰባት አላቂ እና ቋሚ የስፖርት ዕቃዎች፣
- ሎት ስምንት አላቂ እና ቋሚ የላብራቶሪ እቃዎች፣
- ሎት ዘጠኝ የተለያየ አይነት መፅሐፍቶች ሲሆኑ በዚህ መሰረት እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር ወይም ከአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት የታደሰ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት ቲን ነምበር እና ጨረታን ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ቢሮ ቁጥር 34 የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ መረከቢያ ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 9 ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ቫትን ጨምሮ የእያንዳንዱን ዋጋ በግልፅ ማስፈር አለባቸው።
5. ጨረታውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ 33,000 ብር ለሎት ሁለት እና ሎት ሦስት ለእያንዳንዱ 20,650 ብር ለሎት አራት አና ለሎት አምስት ለእያንዳንዱ 18,000 ብር ለሎት ስድስት 9,000 ብር ለሎት ሰባት 16,800 ብር ለሎት ስምንት 8,500 ለሎት ዘጠኝ 8,000 CPO የሚመለስ በመስሪያ ቤቱ ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከቢሮ ቁጥር 04 መግዛት የሚችሉ ሲሆን መ/ቤቱ የሸጠውን የመደበኛ የጨረታ ሰነድ ክፍት ቦታዎች ተሞልቶና እያንዳንዱ ገፅ ላይ ተፈርሞና በማህተም ተረጋግጦ መመለስ ይኖርበታል።
7. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከስራ ሂደቱ ጋር በሚገባው ውል መሰረት ዕቃዎቹን እንዲያስገባ ሲታዘዝ አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በጠቅላላዉ ባሸነፈዉ ዋጋ 10% የሚመለስ በመስሪያ ቤቱ ስም CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
8. በዚህ ጨረታ ላይ የሚቀርብ ማንኛውም የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ ለ60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
9. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
10. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ናሙና ለተጠየቁት ዕቃዎች ከጨረታው ማብቂያ ሰዓትና ቀን በፊት ናሙናዎቹን ማቅረብ ይኖርበታል።
11. የጨረታው ሳጥን በ11ኛ ቀን በ3፡00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የት/ት ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት /ድርጀቶች, ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውሰጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው 2ኛ እና 3ኛ የወጣውን ተወዳዳሪ ሊጋብዝ ይችላል።
13. በመ/ቤታችን ለዕቃ ግዥ በወጣው ጨረታ መሰረት ያለዘርፉ ለመወዳደር ሰነዱን ሞልቶ ያቀረበ ድርጅት ከጨረታዉ ይሰረዛል።
14. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት የዕቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት።
15. አልፎ አልፎ የተመለከቱት የዕቃዎች ልዩ መለያ በጠያቂ መ/ቤቶች ፍላጎት መሰረት ብቻ የዕቃውን የጥራት ደረጃ ለማመልከት የቀረበ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች ተመሳሳይና ከነዚህ የተሻሉ ዕቃዎችን ማቅረብ ይችላል።
16. ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ አብሮ መቅረብ ይኖርበታል።
17. በመ/ቤታችን ለዕቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ።
18. ማንኛውም ተጫራች ከዚህ መመሪያ ውጪ ለማሸነፍ ቢሞክር ወድያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል ያስያዘውም ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
19. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችሉት በሚያመርቱት ምርት ላይ ብቻ መወዳደር ይችላሉ እናም አምራች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የዋስትና ደብዳቤውን የሚወዳደሩትን ሎት እያንዳንዱን በመጥቀስ ዋስትና መግባታቸውን ከአደራጁ ተቋም የበላይ ኃላፊ ዋስትናው ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል።
20. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251 11 835 7484/ +251 11 835 7476 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ ከሆላንድ ኤምባሲ ጀርባ ቀራንዮ መ/ዓለም ቤተ-ክርስቲያን መግቢያ(ቀራንዮ አደባባይ)
በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ የቀራንዮ መ/ዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን በ3፡00
- Bid opening: 2026-09-08 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን በ3፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T09:01:36.000Z