Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

 ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/011/2018

ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን የፅዳት ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ላይ ለመግዛት ይፈልጋል።

የዕቃው እይነት

የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ዋስትና መስከበሪያ

የፅዳት እቃዎች

ነሐሴ 30 ቀን 2018 . 400 ሰዓት

ነሐሴ 30 ቀን 2018 . 430 ሰዓት

30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር

  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨ.እ.ታ፣ የግብር ከፋይ መ/ቁጥር እና ከገቢዎች ባለስልጣን ጽ/ቤት ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ የሚል ማስረጃ ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
  3. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000149984384(££U N/A/A/R CU CON FOR EL CON) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  5. አድራሻ፡-ፒያሳ አቡነጴጥሮስ ፊት ለፊት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-210 በሚገኘው ሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ግዥ እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በአንድ ላይ በማድረግ «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ሰሜ/አ/አሪ/ግ/ጨ/011/2018 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  8. ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 84 82 00 07 መደወል ይችላሉ።
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 የሰሜን አዲስ አበባ ሪጅን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-05 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopia Electrical Utility North Addis Ababa District
  • Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
  • Posted at: 2026-08-27T09:09:38.000Z
← Back to all tenders