Stationery
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ለከተማ አቀፍ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት ለከተማ አቀፍ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን ማለትም፡-
- ሎት-1- እስቴሽነሪ፣
- ሎት-2 ፈርኒቸር፣
- ሎት-3-ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት-7 የሞተር ሣይክል የመብራት ፖዉዛ ዕቃዎች ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩት ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከላይ በዝርዝር የተቀመጡትን መስፈርቶችን - የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሠነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 400 ብር/አራት መቶ ብር/በገደብ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመክፈል ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ከግዥ ክፍል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፤ ቫትን ያላካተተ ከሆነ ቫትን እንደተካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ፦
- ለእስቴሽነር 90,000 ሺህ ብር ፣ፈርኒቸር 75,000 ሺህ ብር
- ለኤሌክትሮኒክስ 235,000 ሺህ ብር፣ የሞተር ሣይክል ግዥ-195,000 ሺህ ብር፣የመብራት ፖውዛ 204,000 ሺህ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች ዕቃዎች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያዩ ፖስት ካሸጉ በኋላ ከሲ.ፒ.ኦ ጋር በአንድ ትልቁ እናት ፖስታ በስም በማሸግ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ማንኛውንም ዓይነት የጨረታ ሰነድ ስርዝ፣ድልዝ ያለው ተቀባይነት የለም።/አይኖርም/
- በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ የሥራ ቀናቶች በሚቆጠር 30 ቀናት ቦኋላ በሥራ ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከላይ የተገለጹ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆኑ በሚቀጠለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ግዥና ንብ/ አስ/ር ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ነው።
- ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ገደብ ከተማ አስ/ር ሩይናንስ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዝ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ - በስልክ ቁጥር፡- 09 26 50 44 88/ 09 26 06 02 63/ 09 15 93 23 49መደወል ይቻላል ።
በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስ/ር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ የሥራ ቀናቶች በሚቆጠር 30 ቀናት በኋላ በሥራ ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-30 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ የሥራ ቀናቶች በሚቆጠር 30 ቀናት በኋላ በሥራ ቀን የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gedeb City FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T09:12:48.000Z