Stationery
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሴክተሮች የጽህፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ፣ የጽዳት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለሚገኙ ሴክተሮች
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- አላቂ ፣
- የጽዳት፣
- ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር
መመሪያ/Bidders instruction/
ሀ. የተወዳዳሪዎች መመሪያ
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆኖ
ሀ. የዘመኑን ግብር በመክፈል የ2019 የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማስረጃ
ለ. የገ/ኢ/ልማት ሚንስቴር የዕቃ ዓቅራቢነት የምዝገባ ማስረጃ
ሐ. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መወዳደር ይችላሉ ።
- ተጫራቾች ከማንኛውም የሙስናና የብክነት ድርጊቶች ነጻ የሆኑና በፌዴራልና በክልል የወጡትን የግዢ ደንቦች በማክበር ሰነዱ ውስጥ የቀረቡትን ግዴታዎች አምነውበት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን በህገወጥ መንገድ ሊያራምድ የሞከረ ከጨረታው ወጪ ከመሆኑም በላይ ለወደፊቱ በሚካሄዱ ጨረታዎችን ላይ እዳይሳተፉ ተደርጎ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል።
- ተጫራቾች ወደ ጨረታው ለመቅረብ ግዴታዎቻቸውን የተወጡና የተጠየቀውን ስፔስፍኬሽን በማሟላት የወቅቱን ገበያ ያገናዘበ ዋጋ ያቀረበ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች መ/ቤቱ ባቀረበው እቃ ዝርዝር በሙሉ ወይም በሚፈልገውም የእቃ ዝርዘር ላይ መጫረት ይችላል እንጂ ተጫራቹ የተወሰነ እቃ ለይቶ ማቅረብ አይችልም።
- የተወዳሪዎች ሃሳብ ሰነድ ሲቀርብ የእቃው እስፔስፊኬሽን፣ የእቃው አይነት፣ የተመረተበት ሀገር ስም፤ እቃው መለያ ሞዴል ቁጥር የተመረተበት ዓመተ ምህረት /ስፔስፍኬሽን ላይ መገለጽ አለበት።
- አሸናፊ ተጫራቾች ክፍያ ከጨረታው እቃ 50% ገቢ ካደረጉ በኋላ ከጠቅላላው ዋጋ 30% ብቻ መጠየቅ ይችላሉ።
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም። )
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የእቃ አይነት የነጠላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የሚቀርበው ዋጋ የወቅቱን አካባቢ ገበያ ያገናዘበ መሆን ይገባዋል።
- የእቃው ሞዴል ወይም ስዕል ናሙና ከጫረታ ሰነዱ ጋር ይቀርባል።
- መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ጨረታ ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
- አሸናፊ ተጫራች ተወዳዳሪ/ የውድድሩ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ከጨረታ መሰከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይወረሳል።
- የጨረታው የመወዳደሪያ ሃሳብ ሰነድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በተለያዩ አንድ ፖስታዎች ከተፈላጊ መረጃዎች ጋር ተያይዞ በሰም ታሸገ ኢንቨሎፕ ይቀርባል።
- የሚቀርበው ሰነድ ሙሉ አድራሻ የተጻፈበት ሆኖ በሚመለከተው ባለስልጣን የተፈረመበትና በማህተም የተረጋገጠ መሆን አለበት።
- ጨረታው በሸገር ከተማ ሱሉልታ ከ ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ ቤት አንድ/1/ ከ2:30 እስከ 12፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን መወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ የያዘ ፖስታ ጫረታውን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ባይገኙም የጨረታው ሳጥኑ ይከፈታል።
- ሰነዱን ለመመርመርና ለመገምገም የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ መስሪያ ቤቱ ተጫራቾቹ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ላይ መግለጫ መጠየቅ ይቻላል።
- ጨረታውን በመመርመር ሂደት ላይ የተገኘውን የሀሳብ ስህተት ማስተካከል ይቻላል።ድርጊቱ ወዲያው የመወዳደሪያ ሀሳብ ሰነድ ላቀረበው ክፍል ይገለጽለታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የውድድር ሀሳብ መቀየር ማሻሻል ወይም ከጨረታው ውስጥ ራስን ማግለል አይቻልም። አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ የጨረታ ውጤት ከተነገረበት 5-10 ቀን ውስጥ ከግዢው ዋጋ ላይ10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ ወይም /CPO/ በማቅረብ የግዢው ውል መፈረም ይኖርበታል።
- የጨረታው ማስከበሪያ አሸናፊው ከታወቀ ለተሸናፊው ይመለስለታል።
- ለአሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የውል ማስከበሪያውን ገቢ አድርጎ ከጨርስ በኃላ ይመለስለታል።
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከፈጸመ በኋላ በ10 ቀን ውስጥ እቃውን አጠናቆ ማቅረብ አለበት። የጨረታው ዋጋ የጨረታውን ውጤት ከተነገረበት ቀን አንስቶ ዕቃውን ማስረከቢያ ቀን ድረስ ያለምንም ለውጥ መቆየት አለበት።. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፈ እቃዎቹን በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ማውጫና ማውረጃ ችሎ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ ቤት እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሚቀርቡት ዕቃዎች የተቀደዱ፣ የተሰበሩ፤ የተበላሹና ከአገልግሎት ውጪ ከሆነ መሥሪያ ቤቱ አይቀበላቸውም።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልም የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው። የሰነድ መሸጫ የማይመለስ 500 ብር ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 / መቶ ሺህ ብር / በባንክ በተመሰከረለት /ቼከ/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 10 82 15 21 በዚህ ስልክ ቁጥር ደውለው ሚፈልጉትን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
ሸገር ከተማ ሱሉልታ ክ/ከተማ የወሰርቢ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-11
- Bid closing time: 09:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-11 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Weserbi woreda finance office
- Bid bond: 100,000 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T09:19:48.000Z