Textile, Garments and Uniforms
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች (Protective device) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር OSE/NCB/003/2019
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት ዓመት፡- የተለያዩ ደንብ ልብስና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች (Protective device) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገስጽን ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)፣
- የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ሰነድ ሶፍት ኮፒ (Soft copy) መግዣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።
ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፤ ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ፡-
ስ.ቁ 011-416 0309/ 011-466-2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-09-11
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-11 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Oromia Seed Enterprise
- Buyer address: ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
- Posted at: 2026-08-27T09:58:01.000Z