Stationery

በሃገር መከላከያ ሚኒስትር በሜናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ፣ ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች ግዥ፣ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ እና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችና አላቂ መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር A-01/2019

በሃገር መከላከያ ሚኒስትር በሜናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ፍላጎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ
  2. ለስልጠና አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች ግዥ
  3. የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
  4. የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችና አላቂ መለዋወጫ እቃዎች

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ የሆነ ነጋዴ ተጫራች በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ

  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ ሰርትፍኬት- የቫት የምዝገባ ሰርትፍኬት የአቅራቢነት መታወቂያ ሰርት ፍኬት እና ካለፉት 3 ወር የቫት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን ያወዳድራል።
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸውና ከታወቁ የፋይናንስ ተቋሞች በተመሰከረለት ባንኮች CPO እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንት ማስያዝ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልፅ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በመፃፍ ኦርጅናል እና ኮር ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 500.00 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 11፡00 ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በር 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የሜ/ድ ዕዝ ጠ/መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 101 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታው ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሜ/ድ ዕዙ ግዥ ቡድን በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል።
  • ስለሆነም የጨረታው ማስታወቂያው እስከ ነሀሴ 21/ 2018 ዓ.ም እንዲወጣልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 04 36 90 ወይም 09 11 02 50 79 ይደውሉ።

የሜ/ ድ ዕዝ ግዥ ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-06
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-06 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በሃገር መከላከያ ሚኒስትር በሜናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 27, 2026)
  • Posted at: 2026-08-27T10:17:38.000Z
← Back to all tenders