Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

በባሌ ዞን የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

  • የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • የጽዳት እቃዎች፣
  • ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ፕላስቲክ /መገጣጠሚያዎች፣
  • Gl መገጣጠሚያዎች የፕላስቲክ ቧንቧዎች፣
  • የመኪና ጎማዎችና መለዋወጫ፣
  • የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና የውሃ ጥራት መጠበቂያ ኬሚካሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያማሉ ተጫራቾች እንዲወዳዳሩ ይጋብዛል።

1. በጨረታው መሳተፍ የሚያስችል በተሰማራበት ዘርፍ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው።

2. ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣገጠሚያ የሚያቀርብ ተጫራች የውሃ ፈንድ ክፍያ 0.5 % መክፈል ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከሮቤ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 11 መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 2% ጨረታው ከመከፈቱ በፈት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጨረታው ሰነድ በተጠቀሰው መሰረት በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በሙሉ የመጫኛና የማጓጓዣ ወጪውን በመቻል መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው።

9. የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው ተጫራቹ ለማቅረብ ውል የፈረሙባቸውን እቃ ሙሉ በሙሉ በንብረት ክፍላችን ገቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ሲቀርብ ነው።

10. ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፍቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በ10 ቀን ውስጥ መ/ቤት ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።

11. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት አይር ላይ ይውላል።

በተጨማሪ መረጃ በስልክቁጥር፡- 09 66 69 69 74፣ 09 04 44 94 98 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

የሮቤ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-15
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-09-15 09:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰአት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Bale Robe City Water Supply and Sewerage Enterprise
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T08:29:23.000Z
← Back to all tenders