Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልጽ ጨረታ የግዥ ማስታወቂያ
ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም.
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት
- ሎት 1 ቋሚ ዕቃ (የመኪና ጎማ፣ ቪዲዮ ካሜራ እና ሞንታርቦ)
- ሎት 2 እስቴሽነሪ ዕቃዎች
- ሎት-3 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-4 የደንብ ልብስ
- ሎት-5 የግብርና ዘሮች
- ሎት-6 የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት-7 የኪራይ አገልግሎት (መኪና፣ ሞንታርቦ፣ ዲኑ እና ድንኳን ኪራይ አገልግሎት) እና
- ሎት-8 ጥገና አገልግሎት ( ፈርኒቸር ጥገና) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
|
የሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር ዕቃዎች |
የተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር |
|
ሎት-1 |
ቋሚ ዕቃ ( አይሲቲ ዕቃዎች ፣ የመኪና ጎማዎች፣ ጋሪዎች፣ የካሜራ መገልገያዎች እና ሌሎች መገልገያዎች ) |
30000.00 |
|
ሎት-2 |
እስቴሽነሪ ዕቃዎች ( የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች) |
30000.00 |
|
ሎት-3 |
የጽዳት ዕቃዎች |
30000.00 |
|
ሎት-4 |
የደንብ ልብስ |
30000.00 |
|
ሎት-5 |
የግብርና ዘሮች |
5000.00 |
|
ሎት-6 |
የመስተንግዶ አገልግሎት |
10000.00 |
|
ሎት-7 |
የኪራይ አገልግሎት (መኪና፣ሞንታርቦ፣ድንኳን እና ዲኮር ኪራይ) |
10000.00 |
|
ሎት-8 |
የጥገና አገልግሎት (ፈርኒቸርና ኤሌትሮኒክስ) |
10000.00 |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎት የማይመለስ ብር 400 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 305 እየቀረቡ መግዛት ይቻላል።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ዋጋውን የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋጋውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10%ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ እና በተጨማሪ የቢሮ መስተንግዶ አገልግሎት ለምትጫረቱ ነጋዴዎች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. መ/ቤቱ ለጨረታው ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስ ሆነ የመጨመር መብቱ የጠጠበቀ ነው።
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ከመገናኛ ወደ 24 ቀበሌ ኮከብ ህንፃ አጠገብ ወረዳ 05 አስተዳደር በመቅረብ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 ፋ/ጽ/ቤት መጠየቅ ይቻላል።
ስልክ ቁጥር፡-09-05-60-96-79
በአዲስ አበባ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-09 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Woreda 5 FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 400.00 ብር በየሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T09:03:17.000Z