Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2019

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት በወረዳው ላሉ ሴ/መ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፡
  • ሎት 2 የእንስሳት መድሃኒትና ቁሳቁስ፡ 
  • ሎት 3 የቢሮ መገልገያ፡
  • ሎት 4 የጽዳት እቃ፣
  • ሎት 5 የመኪና ጎማ፡
  • ሎት 6 ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 7 ህትመት እና
  • ሎት 8 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በየንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሆነው መጫረት የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች

1. ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)ያላቸው

4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው

5. የግዥ መጠኑ ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

6. የእቃው አይነት ዝርዝር መግለጫ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት ገንዘቡን በመክፈል የጨረታ ሰነዱን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች በምትጫረቱበት ሎት ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሳሪያ የጨረታ ማስከበሪያ 60000 /ስልሳ ሺህ ብር/ ለቢሮ መገልገያ 3000 /ሶስት ሺህ ብር/ ለጽዳት እቃ 4000 /አራት ሺህ ብር/ ለእንስሳት መድሃኒትና ቁሳቁስ ግዥ 16000/ አስራ ስድስት ሺህ ብር/ ፈርኒቸር 10000 /አስር ሺህ ብር/ ኤሌክትሮኒክስ 50000 / ሃምሳ ሺህ ብር/ የመኪና ጎማ 6000/ስድስት ሺህ ብር/ ህትመት 3000/ ሶስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ወይም ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት ታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30/ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታውም በዚሁ ቀን 3፡31/ሶስት ሰአት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ ተዘግቶ 4፡00/አራት ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ውስጥ ይከፈታል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሔራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

11. በጨረታው ተሳታፊዎች ፖስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ወይም ህጋዊ ፊርማችሁን ማስቀመጥ ይኖርባችኋል።

12. በጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ካለ ስለመስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት።

13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል

14. መ/ቤቱ እቃዎችን 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል። ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች በተቋሙ በአካል በመምጣት በማየት መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። አሸናፊውም ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ወረዳው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

15. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 011 688 0408 ወይም 011 688 0330 ላይ መደወል ይችላል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን 3፡31/ሶስት ሰአት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ/
  • Bid opening: 2026-09-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00/አራት ሰአት/
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Moret and Jiru Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:12:41.000Z
← Back to all tenders