Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚሰጡ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለድርጅቱ አገልግሎት የሚሰጡ ከታች በምድባቸው በዝርዝር የተገለጹትን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።

በዚህም መሰረት

  • 1ኛ. ሎት ምድብ አንድ /ለሠራተኛ የልብስ ሳሙና 250ግ ፤የገላ ሳሙና 250ግ እና ሶፍት እንዲሁም A4 ወረቀት
  • 2ኛ. ሎት /ምድብ ሁለት ለቢሮ የሚሆን Electronic ዴስክቶፕ ኮምፕዩተር ፤ፕሪንተርና ላፕቶፕ ኮምፕዩተር ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

3. ከላይ በተጠቀሰው ዕቃ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ እንዲሁም በዘርፉ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ

4. ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒሰቴር የዕቃ አቅራቢ ውሰጥ የተመዘገቡ ሰለመሆናቸው የሚገልፅ የምዝገባ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የግብር ከፍይነት መለያ ቁጥር /TIN/ መኖሩን የሚገልጽ ማስረጃ

5. በሚወዳደሩት የዕቃ ዓይነቶች ለእያናዳንዱ ዕቃዎች ዓይነት ለውድድር ሲመጡ በየአይነታቸው አንዳንድ ሳምፕል ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ተወዳድሮ ሲያሸንፍ ያሸነፋቸውን ዕቃዎችን በራሱ ትራንስፖርት እስከ ድርጅቱ እስቶር ድረስ በማቅረብ የጫኝና አውራጅ ችሎ ማስረከብ የሚችል፡፡

6. ከላይ በሎት አንድ /ምድብ አንድ እና በሎት ሁለት /ምድብ ሁለት በሚወዳደሩት የዕቃ ዓይነት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ cpo ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ዶክመንት ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል ።

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ ከፍሎ ከድርጅቱ በመውሰድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖሰታ/ቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናል ለብቻ ፋይናንሻል ዶክመንት ኮፒ ለብቻ አሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውሰጥ በማስገባት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአርባምንጭ ከተማ ውሃና ፋሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግቢ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል ፡፡ ሆኖም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡ በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም ፡፡

8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 046 881 0369/046 881 2049 መደወል ይቻላል ፡፡

የአ/ምንጭ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Arba Minch Town Water Supply and Sewerage Enterprise
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:28:52.000Z
← Back to all tenders