Stationery

በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/18

በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ለ2019 ዓ.ም ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት.1 አላቂ የቢሮ እቃ የፅሕፈት እቃዎች
  • ሎት.2 አላቂ የፅዳት እቃዎች
  • ሎት.3.ደንብ ልብስ
  • ሎት.4.ቋሚ እቃዎች
  • ሎት.5.የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት.6.ህትመት ስራዎች(ውጤቶች)
  • ሎት.7. ትራንስፖርት አገልግሎት
  • ሎት.8.የጥገና አገልግሎት
  • ሎት.9.የመስተንግዶ አገልግሎት

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
  2. የመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ።
  3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ 2% ማለትም

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና cpo በብር

ሎት.1

20,000

ሎት.2

30,000

ሎት.3

40,000

ሎት.4

40,000

ሎት.5

20,000

ሎት.6

20,000

ሎት.7

15,000

ሎት.8

15,000

ሎት.9

10,000

6. ማንኛውም ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በየሎቱ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ፋ/ፅ/ቤት4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በታሸገ ኢንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ በዛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ላሸነፉበት እቃ ዋስትና ወይም የውል ማስከበሪያ CPO 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. በተጨማሪ መስሪያ ቤቱ የጨረታውን 20% መቀነስ ወይም መጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች ለመጫረት ሲመጡ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፍኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

11. በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመ/ቤቱ ግ/የስራ ሂደት ክፍል ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 011 867 8129 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ ፡- መገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና መሥሪያቤት ፊትስፊት

በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-09 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Sub-City Woreda 06 Finance Bureau
  • Buyer address: ከመገናኛ ወደ ሾላ በሚወስደው መንገድ ገባ ብሎ ውሃ እና ፍሳሽ ባስስልጣን ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:30:27.000Z
← Back to all tenders