Building Construction
በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው አይሶሌሽን ክፍል ግንባታ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው አይሶሌሽን ክፍል ግንባታ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ድረስ በመምጣት ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማይመለስ 200 ሁለት መቶ) ብር በመክፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ ሦስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ዓይነት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው ጨረታ ሳጥን በ16ኛው(አስራ ስድስት)ቀን እስከ ቀን 7፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ Technical proposal / እና ፋይናንሻል ሰነድ /financial proposal / ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን ጠዋት 8:00 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት/technical proposal/ በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ የግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
4. ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND of BID SECURITY) (40,000 ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፋይናንስ አስተዳደር ፑል ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
6. ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ከአንድ ፕሮጀክት በላይ በጨረታ መሳተፍ አይችልም። በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል ።
7. ከትንሹ ግምት በታች እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬክዳውን (BREAKDOWN) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን።
8. ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን በአካል ማቅረብ መረዳት ይቻላል።
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
አድራሻ፡- ፊጋ መብራት ጋር በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ላይ መሆኑን እንገልጻለን።
የወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 13:30
- Bid closing (note): ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው(አስራ ስድስት) ቀን እስከ ቀን 7፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 14:00
- Bid opening (note): ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው(አስራ ስድስት) ቀን ጠዋት 8:00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Amoraw Health Center
- Bid bond: 40,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T09:39:59.000Z