Vehicle and Machinery Sale
የተሽከርካሪ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ነጻነት ኪሮስ እና በፍ ባለዕዳ በለጠ ስዮም መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/177014 በ12/09/2018 ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/177014 በ27/9/2018ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/171332 በ14/08/2018ዓ/ም እናበኮ/መ/ቁ/177014 በ30/10/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁ. ኮድ 3-B91302 ኢ.አ Swift Suzuki ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,572,062.28/100 ( ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሁለት ሺህ ስልሳ ሁለት ብር 28/00) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ5 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11 273 0852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 15:30
- Bid opening: 2026-09-18 15:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Aug 29, 2026)
- Posted at: 2026-08-29T08:23:48.000Z