Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ሥራ አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፣ ደንብ ልብሶች፣
- ሎት 2 የመኪና ጎማዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ
1.ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ከሊራንስ) ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ።
2.ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከገቢዎች ባለሥልጣን በተወከለው ሠራተኛ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ወደ ሲንቄ ባንክ ሂሳቢ ቁጥር በSebeta Sub city Finance office “A” 1064814111214 ገቢ በማድረግ ክፍለ ከተማ ገቢዎች በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት በሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት መግዛት ይቻላል።
3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎቶች በተዘጋጀው ሰነድ ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
6. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ መስፈር አለበት።
7.ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባችዋል።
8. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱ በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል።
9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ከስቶክ ወይም ከራሳቸው ስቶር መሆን ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ የሎት አንድ (1)2 ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው።
12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
13. ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የሥራ ቀን ይሆናል።
14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113662199 (0913658563)
የሰበታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City High Court Sebeta Sub City Woreda Court
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T08:00:11.000Z