Building Construction
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
1፡- በዞብል ክ/ከተማ የአቅመ ደካማ ቤት ግንባታ ስራ ለማሰራት ከደረጃ 8 በላይ የሆኑ ከላይ የተዘረዘሩትን ስራዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሞሉ ተጫራቾች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN /ያለው/ ያላት
3. ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ /A/ ተመዝጋቢ የሆነ/ የሆነች የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታ ሲያስገቡ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
5. የሚሰሩ ስራዎች ዓይነትና እስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺ/ ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 21 ማግኘት ይችላሉ
8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጎ/ከ/አስ/ከ/መ/ል/መምሪያ ግዥናፋ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ24/12/2018 ዓ.ም እስከ 9/1/2019 ዓ/ም ድረስ ሲሆን መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ4፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ይከፈታል።
10. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ የሥራው ዝርዝር ዋጋ ሙሉ በሙሉ መሞላት አለበት ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ደግሞ ውድቅ ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገዎት ጎ/ከ/አስ/ከ/ስ/ኮ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር O6 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 71 20 38 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና
መሰረተ ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-21 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gonder City Admnstarion City Urban Development office
- Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T08:02:57.000Z