Stationery

የጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ስቴሽነሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ስቴሽነሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፦

1. ተጫራቾች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉና ፍቃዳቸውን ያደሱ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ እና ህጋዊ ማስረጃቸውንና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።

4. የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩ ዕቃዎች ዝረዝር በሙሉ አቅም የሚያቀርቡ ሆኖ ለየትኛውም ዐይነት ዕቃ ናሙና ሲጠየቁ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለእስቴሽነሪ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO /በካሽ/ በእንደጋኝ ወረዳ ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ከግ/ን/አስ/ስ/ሂደት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት በመቅረብ በዋጋ ማቅረቢያችሁ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል በመ/ቤታችን ስም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኃላ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ስዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበተት በዚያው ዕለት በ8፡30 ሰዓት ላይ በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የግዥ ኮሚቴ ቢሮ ወይም በሚመቻች ክፍል ይከፈታል።

9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።

10. አሸናፊው ድርጅት እቃውን የሚያሰረክበው የእ/ፋ/ጽ/ቤት ድረስ በማቅረብ ይሆናል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 350 00 47/46

በጉራጌ ዞን የእንደጋኝ ወረዳ ፋይናስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ስዓት
  • Bid opening: 2026-09-14 14:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ስዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Endegagn Wereda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 30,000.00 ብር
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ የማይመለስ 500 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T08:43:52.000Z
← Back to all tenders