Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፈሊጶስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፈሊጶስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ.ም የስራ ዘመን የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-
- ሎት 1 የፅህፈት እቃዎች ግዥ
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥ
- ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
- ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች ግዥ
- ሎት 6 የህትመት ግዥ
- ሎት 7 የጭነት አገልግሎት ግዥ
- ሎት 8 የችግኝ ግዥ
- ሎት 9 የመፅሀፍት ግዥ
ከላይ በሎት የተዘረዘሩት እቃዎች ድርጅታችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል ።
1. የንግድ የምዝገባ ምስክር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ታክስ ኪሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
4. የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
5. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
6. የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
7. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
8. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት በአዋጁ መሠረት የተቋቋሙ አምራች በሆኑበት ዘርፍ ብቻ ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9.ተጫራቾች መደበኛው የጨረታ ሰነድ ሳይገነጠል በሙሉ ተመላሽ ማድረግ አለባቸው
10 . ተጫራቾች ከጨረታ መዝጊያ ሶስት (3) ቀናት በፊት ቀደም ብለው ለሚጫረቱባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
11. እስከ መስሪያ ቤቱ ድረስ ለማምጣት ቀላል እና ለማንቀሳቀስ ከባድ ያልሆኑ እቃዎች ሳምፕል በአካል መቅረብ ይኖርባቸዋል።
12. በፎቶ የሚቀርቡ ናሙናዎች ከለር ፕሪንት ሆነው ስለ እቃው ግልፅ የሆነ የፅሁፍ ማብራሪያ (እስፔሲፊኬሽን) ያለው መሆን አለበት።
13 ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO, ሎት 1, 10,000 (አስር ሺ ብር) ፣ ሎት.2, 10,000 (አስር ሺ ብር)፣ ሎት.3, 25,000 (ሀያ አምስት ሺ ብር)፣ ሎት.4, 40,000 (አርባ ሺ ብር)፣ ሎት.5, 25,000 (ሀያ አምስት ሺ ብር)፣ ሎት.6, 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) ፣)፣ ሎት7, 5,000 (አምስት ሺ ብር)፣ ሎት 8 10,000 (አስር ሺ ብር) ፣ ሎት.9, 5,000 (አምስት ሺ ብር) ሲሆን ከዚህ ውጪ የሚቀርብየጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
14. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ 4ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 68 መጥተው መግዛት ይችላሉ።
15. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ብቻ የመጫረቻ ሰነዳቸው መስሪያ ቤቱ ለዚህ አገልግሎት ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥንውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
16 .በ11ኛው ቀን የሚመጣ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
17. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጨረታ ኮሚቴ እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ታሽጎ በዛው እለት ወዲያውኑ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
18. መ/ቤቱ በጨረታ ከቀረበው የእቃ ብዛት እስከ 20% መቀነስም ሆነ መጨመር ይችላል ።
19 .መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
20 .በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ኦርደር ከተሰጠው ከሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ የጠቅላላ ዋጋው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መግባት ይኖርበታል።
21. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ፋይናንሻል ኦርጂናልና ፋይናንሻል ኮፒ፣ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ፣ ለየብቻ በካኪ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም አድርገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
22. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈው እቃ በራሱ ትራንስፖርት እስከ መስሪያ ቤት የሚያቀርብ ይሆናል።
23 . አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈው እቃ የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርሰንት) አሲዞ ውል ሳይገባ እቃ ወደ መስሪያ ቤት ማምጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው።
24. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ኦርደር ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
አድራሻ፡- ከኮልፌ አጠና ተራ ወደ ስሚ-ሜዳ በሚወስድው መንገድ/ ፊሊጶስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት እንገኛስን። ስ.ቁ፡-011-2-73-92-45
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 11 ፊሊጶስ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Philipos Health Post
- Buyer address: ኮልፌ አጠና ተራ ፊሊጶስ ቤ/ክ ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T09:08:34.000Z