Stationery

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ መገልገያ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የእቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መገልገያ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት1- የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
  • ሎት-2- የጽዳት እቃዎች ግዥ
  •  ሎት-3- የሰራተኛ የደንብ ልብስ ግዥ
  • ሎት.4.የበርና የመሳቢያ ቁልፎች
  • ሎት.5. የመስተንግዶ አቅርቦት ግዥ/ውሃ ቆሎ ወዘተ/
  • ሎት-6 የሰራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት ግዥ
  • ሎት.7. የተለያዩ ትራንስፖርት አቅርቦት ግዥ
  •  ሎት 8 የህትመት ስራዎች ግዥ
  •  ሎት 9 የኤሌትሪክ እቃዎች ግዥ
  •  ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ባለሙያ ግዥ
  •  ሎት 11 የቢሮ ቋሚ እቃዎች ግዥ ወዘተ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
  1. ተጫራቾች በሙያው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ እና ወቅታዊ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡-
  2. በመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በኤሌክትሮኒክስ አቅራቢነት ሊስት በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  4. የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 600 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡
  5.  የጨረታ ሰነዶቻችሁን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመሙላት ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳደንዱ ለተጫረቱበት ሎቶች 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 2 አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7.  የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በመሙላት በኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ከገዙበት ጨረታ ሰነድ የዋጋ መሙያ ፎርም ውጭ ዋጋ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. ለሚያቀርባቸው እቃዎች እና ዋስትና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ዋስትና ማቅረብ የሚችል
  10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ከጎጃም በረንዳ በዮሃንስ የሚወስደው መንገድ አራት መንታ ሐገቤስ አከባቢ

በስልክ ቁጥር 0111-55-32-16/ 0111-26-54-20

የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 600.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
  • Posted at: 2026-08-31T09:23:18.000Z
← Back to all tenders